አሜሪካ ለዩክሬን ከ5 ሺህ በላይ ክላሽ የተሰኘ የጦር መሳሪያ ሰጠች
ለዩክሬን የተሰጡት ጦር መሳሪያዎች ኢራን ለሁቲ ታጣቂዎች በማጓጓዝ ላይ እያለች የተያዘ ነው ተብሏል
ኢራን በበኩሏ ለሁቲ ታጣቂዎች ሳጓጉዝ የተያዘብኝ ጦር መሳሪያ የለም ስትል አስተባብላለች
አሜሪካ ለዩክሬን ከ5 ሺህ በላይ ክላሽ የተሰኘ የጦር መሳሪያ ለዩክሬን ሰጠች፡፡
የአሜሪካ ማዕከላዊ እዝ በኤክስ የማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰራጨው መግለጫ በተለያዩ ጊዜያት ለሁቲ ታጣቂዎች ሊሰጥ የነበሩ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን መያዙን አስታውቋል፡፡
የጦር መሳሪያዎቹ ሰንደቅ አላማ በሌላቸው መርከቦች ተጭነው ወደ የመን በማምራት ላይ እያሉ እንደተያዙ የተገለጸ ሲሆን ከኢራን የመጡ ሊሆኑ እንደሚችሉም ተገልጿል፡፡
ከተያዙት ጦር መሳሪያዎች መካከል በተለምዶ ክላሽ በመባል የሚታወቀው የጦር መሳሪያን ጨምሮ ከ500 ሺህ በላይ የተለያዩ ጦር መሳሪያ ጥይቶች እና ሌሎች የቡድን መሳሪያዎችም እንደሆኑ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
አሜሪካ እነዚህን ጦር መሳሪያዎች ለዩክሬን አሳልፋ እንደሰጠች የተገለጸ ሲሆን ዩክሬንም በተሰጣት ጦር መሳሪያ ድጋፍ አንድ ብርጌት ወይም እስከ 5 ሺህ የሚደርስ ተዋጊዎችን ለማስታጠቅ ትጠቀምበታለች ተብሏል፡፡
ኢራን በበኩሏ በአሜሪካ ተያዘ እና ለዩክሬን ተላልፎ ተሰጠ የተባለው የጦር መሳሪያ እንደማይመለከታት እና የራሷ ባልሆነ የጦር መሳሪያ ላይ አስተያየት አልሰጥም ማለቷ ተገልጿል፡፡
አሜሪካ እስካሁን ለዩክሬን የሰጠችው የገንዘብ እና ጦር መሳሪያ ድጋፍ ከ60 ቢሊዮን ዶላር በላይ የደረሰ ሲሆን ተጨማሪ ድጋፍ ለማድረግ የምክር ቤት አባላት ክርክር እያደረጉበት ይገኛሉ፡፡
ሪፐብሊካን ፓርቲን ወክለው የአሜሪካ ምክር ቤት አባላት የፕሬዝዳንት ባይደን አስተዳድር ለዩክሬን የተጋነነ ድጋ እየተደረገ ነው በሚል ተጨማሪ ገንዘብ ድጋፍ እንዳይደረግ ተቃውሞ እያሰሙ ናቸው፡፡
ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ አሜሪካ ድጋፍ ካላደረገች ዩክሬን መሸነፏ እና ሩሲያ ወደ ዋና ዋና ከተሞች መግባቷ እንደማይቀር ተናግረዋል፡፡
ኢራን በአሜሪካ ላይ ጥቃት እንዳትሰነዝር መጠየቋን ገለጸች
የፕሪታንያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩን ወደ አሜሪካ ተጉዘው ከሪፐብሊካን ፓርቲ እጩ ዶናልድ ትራምፕ እና ሌሎች የምክር ቤት አባላት ጋር ተመካክረው መመለሳቸውም በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
የዩክሬን ሽንፈት ለአውሮፓ እና አሜሪካ ደህንነት ስጋት እንደሚሆን ዴቪድ ካሜሩን ለዶናልድ ትራምፕ እንደነገሯቸው ይህ እንዳይሆን አሜሪካ ተጨማሪ የጦር መሳሪያ ድጋፍ እንድታደርግ ማግባባታቸውም ተገልጿል፡፡