በቻይና ከባለፈው ሳምንት ወዲህ የሙቀት መጠኑ ከ40 ዲግሪ ሴንትግሬ አልፏል
ክብረወሰን በሰበረ ሙቀት እና ድርቅ ውስጥ ያለችው ቻይና ከደመና ዝናብ ለማዝነብ ሮኬትና ድሮን ማሰማራቷን ስካይ ኒውስ ዘግቧል።
ወደ ደመና የተላከው መሣሪያ ከበረዶ ጋር ተመሳሳይ ቅርጽ ያለውን ሲልቨር አይዎዳይድ የሚረጭ ሲሆን በደመናው ላይ ሲበተን የዝናብ መከሰት እድልን ይጨምራል።
ይህ ተግባር ደመናን ማበልጸግ ወይም ክላውሲዲንግ የሚባል ሲሆን ቻይና የዝናብ ፍሰት እና መቀት መጠን መመዝገብ ከጀመረችበት ከፈረንጆቹ 1961 ጀምሮ በድርቅ እና በሙቀት ወቅት ስትጠቀምበት ነበር።
በቻይና ከባለፈው ሳምንት ወዲህ የሙቀት መጠኑ ከ40 ዲግሪ ሴንትግሬ አልፏል። በደቡባዊ ቻይና የምትገኘው የጓንዙ ግዛት የዌዘር ሞዲፊኬሽን ኦፊሰር የሁዋንግ ሆጃን ሁሉንም የግዛቱን ቦታ ለመሸፈን ስምንት በሪራዎች ለማድረግ ታቅዶ እንደነበር ገልጸዋል።
የዝናብ መጠን ለመጨመር በጄቶች ብዙ ኦፐሬሽን እንደሚካሄድ ገልጸዋል።