አሜሪካዊው ጆይ ቼስትኑት በ8 ደቂቃ ውስጥ 32 ጣሳ ፋንዲሻ በመመገብ አዲስ ክበረ ወሰን አሰመዘገበ
ክብረወሰን በመስበርም ምር የ“ፖፕኮርን ቻሌንጅ” ውድድር ያሸነፈው ቼስትኑት፤ 450 ሺህ ዶላር ተሸልሟል
ቼስትኑት፤ በውድድሩ “በማኘክ ምክንያት በጉሮሮዬ ላይ ህመም ተሰማኝ ”ሲል ተናግሯል
የ39 አመቱ አሜረካዊው ጆይ ቼስትኑት “በ8 ደቂቃ ውስጥ 32 ጣሳ ፋንዲሻ በመመገብ” አዲስ ሪከርድ አሰመዘገበ፡፡
"ጃው"ወይም “መንጋጋ” በሚል ቅጽል ስም የሚታወቀው ቼስትኑት በዓለም ላይ በርካታ የመብላት ፈተናዎችን እና ውድድሮችን በማሸነፍ ስሙ የናኘ ነው፡፡
በዚህም ባለፈው ረቡዕ እለት በአሜሪካ ኢንዲያናፖሊስ ከተማ በተካሄደው ዓለም አቀፍ ውድድር ቼስትኑት እያንዳንዳቸውን 680 ግራም የሚገመቱ የ32 ጣሳዎች ፋንዲሻ በመብላት ስራውን በ8 ደቂቃ ማጠናቀቅ መቻሉ በርካቶችን አስገርሟል፡፡
ይህም ቀድም ሲል በራሱ ተይዞ የነበረውን የ28 ነጥብ 5 ጣሳዎች ፋንዲሻ የመብላት ክበረ ወሰን መስበር እንደቻለ እየተነገረ ነው፡፡
በዚህም የ“ፖፕኮርን ቻሌንጅ” ተብሎ የሚታወቀው ውድድር ያሸነፈው ቼስትኑት፤ 450 ሺህ ዶላር እንደተሸለመ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል፡፡
ከውድድሩ በኋላ ይህን ከፍተኛ መጠን ያለው ፋንዲሻ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመብላት ስለተከተለው እቅድ የተናገረው ቼስትኑት “ፋንዲሻውን በፍጥነት ለማኘክ ውሃ ለመጠጣት ጓጉቼ ነበር፣ ከዚያ በኋላ አዲስ መጠን ለመጨመር …. ወዘተ” ብሏል፡፡
“በማኘክ ምክንያት በጉሮሮዬ ላይ ህመም ተሰማኝ፣ነገር ግን ችግሩን በውሃ በመጠጣት አሸንፌዋለሁ” ሲልም አክሏል፡፡
ቼስትኑት ከዚህ ቀደም እንደ “ሆት ዶግስ” ባሉ በርካታ ፈጣን የመብላት ውድድሮች ማሸነፉ እንዲሁም በ2021 በአሜሪካ ላስ ቬጋስ በተካሄደው የተመዘገበውን ፋንዲሻ የመመገብ ውድድር ሪከርድ መስበሩ አይዘነጋም፡፡
ጆይ ቼስትኑት፤ በእንዲዘህ አይነት ያልተለመዱ ውድድሮች መሳተፍ ከጀመረ አንስቶ ክብደቱ ከ102 እስከ 109 ኪሎ ግራም እንደሚመዘን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
ቼስትኑት እንደረንጆቹ 2012 ስድስተኛው ተከታታይ ውድድሩ ባሸነፈበት ወቅት “70 አመት እስኮሀነኝ ድረስ ውድድሩን አላቆምም፤ ይህ ስፖርት ስለ መብላት አይደለም ፤ስለ አመራርና ራስን መወሰን ነው” ያለበት አጋጣሚ የታወሳል፡፡