“ዶንግፌንግ” የቻይና የሚሳዔል እስከ 12 ሺህ ኪ.ሜ የሚጓዝና አሜሪካን መምታት የሚችል ነው
ቻይና የማይታዩ የዶንግፌንግ የሚሳዔል ማስወንጨፊያዎችን እየሰራች መሆኑ ተገለጸ።
አዲሱ የቻይና የሚሳዔል ማስወንጨፊያ በቀላሉ በሳተላይት፣ በራዳር እና በድሮኖች የማይታይ መሆኑ ተነግሯል።
የቻይና እቅድ ሀገሪቱ ወደፊት ለሚኖሩ ጦርነቶች የአዲስ ትውልድ የጦር መሳሪያዎችን የማበልጸግ አካል መሆኑን የቻይናዊ ሲሲቲሺ ቴሌሺዥን ጣቢያ የቻይና ጦር ማዘመንን አስመልክቶ ባሰራጨው ዘጋቢ ፊልም ላይ ተጠቅሷል።
በቻይና ጦር ተመራማሪ የሆኑህ ያንግ ባዮ፣ አዳዲሶቹን የቻይና የሚሳዔል ማስወንጨፊያ ለመስራት አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ጥቅም ላይ መዋላቸውን አስታውቀዋል።
"ወደፊት በሚኖሩ አውደ ውጊያዎች ጠላቶቻችን ቻይና ሚሳዔል ከየት እንድምታስወነጭፍ እንደማያውቁ እምነት አለኝ" ሲሉም ተናግረዋል።
ለቻይና ጦር ቅርብ የሆኑ የመረጃ ምንጮች እንደጠቆሙት ከሆን ከእይታ ውጭ መሆን የሚችሉት የሚሳዔል ማስወንጨፊያ ተሽከርካሪዎች "DF-17 እና DF-16B" የተባሉ ሚሳኤሎችን ለማስወንጨፍ የሚውሉ ናቸው።
"DF-17 እና DF-16B" የባላስቲክ ሚሳዔሎች ሲሆኑ፣ መካከለኛ ርቀት ኢላማ የሚመቱ እና በተለይም በታይዋን ላይ የሚደረግ የውጭ ጣልቃ ገብነትን ለመመከት ታልመው የተሰሩ እንደሆነ ተነግሯል።
እንዲሁን ስውሩ የቻይና ሚሳዔል ማስወንጨፊያ መርሃ ግብር "DF-17" ሚሳዔሎችን እንዲሁም "DF-41" የተባለ ጠንካራ የባላስቲክ ሚሳዔሎችን ያድወነጭፋል ተብሏል።
"DF-41" የተባለው የቻይና አህጉር አቁዋራጭ ሚሳዔል እስከ 12 ሺህ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ያለን ኢላማ መምታት የሚችል ሲሆን፣ ይህም በአሜሪካ ውስጥ የሚገኝ ማንኛውንም ኢላማ የመምታት አቅምን አስታጥቆታል።
"DF" የሚል መጠሪያ ያላቸው የቻይና ሚሳዔሎች የኮንቬንሺናል እንዲሁም የኒውክሌር አረር የመሸከም አቅም ያላቸው የሚሳዔል አይነቶች መሆናቸው ይነገራል።