ሰሜን ኮሪያ አሜሪካን መምታት የሚችሉትን የረጅም ርቀትን ጨምሮ እስከ አጭር ርቀት ሚሳኤሎችን ታጥቃለች
ስሟ በተደጋጋሚ ከጦር መሳሪያ ሙከራዎች ጋር ተያይዞ የሚነሳው ሰሜን ኮሪያ ከረጅም ርቀት እስከ አጭር ርቀት ተወንጫፊ የሚሳዔል አይነቶች እንደታጠቀች ይነገራል።
ሀገሪቱ በትናትናው እለት በጃፓን የአየር ክልል በኩል ወደ ፓስፊክ ውቂያስ የተኮሰችው ሚሳዔል ከመውደቁ በፊት 4 ሺህ 500 ኪሎ ሜትሮችን እንደተጓዘ ታውቋል።
ሰሜን ኮሪያ ባለንበት የፈረንጆቹ 2022 ብቻ ከ30 በላይ የሚሳዔል ማስወንጨፍ ሙከራዎችን ያደረገች ሲሆን፤ አሜሪካን መምታት የሚችሉንትን የረጅም ርቀት ሚሳዔል ጨምሮ እስከ አጭር ርቀት ሚሳዔል ድረስ ሙከራዎችን አድርጋለች።
ሀገሪቱ በትናትናው እለት በጃፓን ሰማይ ላይ ያስወነጨፈችው ሚሳዔል “ሃውሶንግ 12” በመባል የሚጠራ ሲሆን፤ እስከ 4 ሺህ 500 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ማጥቃት የሚችል እና የአሜሪካዋ ጉዋም ደሴትን መምታተ የሚችል ነው ተብሏል።
ሀገሪቱ ሙከራ ያደረገችባቸው የሚሳዔል አይነቶችም ውስጥም ባላስቲክ ሚሳዔል፣ ክሩዝ ሚሳዔል እና ሃይፐርሶኒክ ሚሳዔል ይገኙበታል።
ሃይፐርሶኒክ ሚሳዔል የራዳር ቁጥጥርን መጣስ የሚችል እና ከድምጽ በብዙ እጥፍ የሚፈጥን የመሳሪያ አይነት መሆኑ ይታወቃል።
ሰሜን ኮሪያ ያላት የሚሳዔል አይነት እና የሚጓዙት ርቀት
ኖዶንግ 1 ሺህ 500 ኪሎ ሜትር
ፑክጉክሶንግ-3 1 ሺህ 900 ኪሎ ሜትር
ፑክጉክሶንግ-2 2000 ኪሎ ሜትር
ሙሱዳን 4000 ኪሎ ሜትር
ሃውሶንግ-12 4 ሺህ 500 ኪሎ ሜትር
ሃውሶንግ-14 10 ሺህ 400 ኪሎ ሜትር
ሃውሶንግ-15 13 ሺህ ኪሎ ሜትር
ሃውሶንግ-17 ከ15 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ
ሰሜን ሃውሶንግ በመባል የሚታወቁት የአህጉር አቋራጭ የባላስቲክ ሚሳኤሎች ላይ ተደጋጋሚ ሙከራዎች እያደረገች መሆኑ ይታወቃል።
ለአብነትም ሃውሶንግ-14 የሚል መጠሪያ ያለው አህጉር አቋራጭ የባላስቲክ ሚሳኤሎች ከ8 ሺህ እሰከ 10 ሺህ ኪሎ ምትር ድረስ ማጥቃት የሚችል ሲሆን፤ ይህም የአሜሪካዋ ኒውዮርክ ከተማን የመምታት አቅም ያለው መሆኑን ከጃፓን መከላከያ ሚኒስቴር ሲ.ኤስ.አይ የሚሳዔል መከላከያ ፕሮጅከት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።