የቻይና ምርት የሆነው “C919” የመንገደኞች አውሮፕላን ለመብረር የሚያስችለውን ፈቃድ አገኘ
የቻይና ወደ ገበያው መግባት ለአሜሪካው ቦይንግና ለፈረንሳዩ ኤር ባስ አዲስ ፈተናን ይዞ ይመጣል ተብሏል
“C919” የቻይና አውሮፕላን ከ158 እስከ 168 መቀመጫዎች ያሉት ሲሆን፤ በሰዓት እስከ 900 ኪ.ሜ መብረር ይችላል
ቻይና በራሷ አቅም ያመረተችው የመጀመሪያ የመንገደኞች አውሮፕላን ለመብረር የሚያስችለውን ፈቃድ ማግኘቱ ተነግሯል።
C919” የመንገደኞች አውሮፕላን በቻይና ሲቪል አቪዬሽን አስተዳደር ባሳለፍነው ሳምንት “የአየር ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት” እንደተሰጠው ተነግሯል።
አውሮፕላኑ በመካከለኛ ደረጃ የሚመደብ ሲሆን፤ `C919` የሚል ስያሜ የተሰጠው አዲሱ የቻይና አውሮፕላን ወደ ገበያ ሲቀላቀል ለእነዚህ ግዙፍ የአውሮፓላን አምራቾች አዲስ ተፎካካሪ ይሆናል ተብሏል።
በተለይም የቻይና “C919” የመንገደኞች አውሮፕላን ከቦይንጉ 737 ማክስ እና ከኤርባስ A320 ጋር የሚፎካከር መሆኑን ሲ.ጂ.ቲ.ኤን ዘግቧል።
“C919” አውሮፕላን ከ158 እስከ 168 መቀመጫውች ያሉት ሲሆን፤ እስክ 12 ሺህ 100 ሜትር ከፍተታ ድረስ መብረር የሚችል መሆኑም ነው የተገለፀው።
በሰዓት እስከ 900 ኪሎ ሜትር የሚበረው አውሮፕላኑ፤ በአንድ ጊዜ ከ4 ሺህ 75 እስከ 5 ሺህ 555 ኪሎ ሜትር መብረር የሚችል መሆኑም ተነግሯል።
ቻይና ኢስተርን አየር መንገድ አምስት `C919` የመንገደኞች አውሮፕላን ከቻይና የንግድ አውሮፕላን ኮርፖሬሽን ለመግዛት መፈራረሙ ታውቋል።
መቀመጫውን ሻንጋይ ያደረገው የቻይና የንግድ አውሮፕላን ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ እንደተናሩት፤ አሁን ላይ አውሮፕላኖቹ እየተመረቱ መሆኑን ጠቅሰው፤ በያዝነው የፈረንጆቹ ዓመት አውሮፕላኑ እንዲመረትላቸው ላዘዙ ተቋማት ርክክብ ማድረግ እንደሚጀመር አስታውቀዋል።
የአውሮፕላን ምርት እንዲስትሪው በቢሊየን ዶላሮች የሚንቀሳቀስ ሲሆን፤ የአሜሪካው ቦይንግ እና አፈረንሳዩ ኤር ባስ ይህንን ኢንደስትሪ በበላይነት እንደሚመሩት ይታወቃል።