ቻይና፤ አሜሪካ የተኩስ አቁም የውሳኔ ሀሳብ እንዳይጸድቅ ማድረጓ "ከፍተኛ ቅሬታ" እንደፈጠረባት ገለጸች
አሜሪካ በምክርቤቱ የቀረበ የተኩስ አቁም የውሳኔ ሀሳብ እንዳይጸድቅ ስታደርግ ይህ ለሶስተኛ ጊዜ ነው
እስራኤል እና አጋሯ አሜሪካ ተኩስ አቁም ሀማስ መልሶ እንዲደራጅ ያደርገዋል በሚል ምክንያት አይቀበሉትም
ቻይና፤ አሜሪካ የተኩስ አቁም የውሳኔ ሀሳብ እንዳይጸድቅ ማድረጓ "ከፍተኛ ቅሬታ" እንደፈጠረባት ገለጸች።
አሜሪካ በተመድ የጸጥታው ምክር ቤት በጋዛ ተኩስ አቁም እንዲደረግ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ ቬቶ ወይም ድምጽን በድምጽ የመሻር መብቷን ተጠቅማ እንዳይጸድቅ በማድረጓ ቻይና "ከባድ ቅሬታ" ማሰማቷን ሮይተርስ ዘግቧል።
አሜሪካ በምክርቤቱ የቀረበ የተኩስ አቁም የውሳኔ ሀሳብ እንዳይጸድቅ ስታደርግ ይህ ለሶስተኛ ጊዜ ነው።
አሜሪካ በአልጀሪያ የቀረበው የወሳኔ ሀሳብ፣ በአሜሪካ፣ በግብጽ፣ በእስራኤል እና በኳታር መካከል ጦርነቱን ጋብ ለማድረግ እና ታጋቾችን ለማስለቀቅ እየተካሄደ ያለውን ሚስጥራዊ ድርድር አደጋ ላይ የሚጥል ነው የሚል ምክንያት አቅርባለች።
ቻይና የተኩስ አቁም የውሳኔ ሀሳቡን አሜሪካ እንዳይጸድቅ በማድረጓ ከፍተኛ ቅሬታ እንደተሰማት ሮይተርስ ሽንዋን ጠቅሶ ዘግቧል።
ቻይና እንደገለጸችው አሜሪካ የውሳኔ ሀሳቡ እንዳይጸድቅ ማድረጓ በጋዛ ያለው ሁኔታ እንዲባባስ እና ግድያውን እንዲቀጥል የሚያደርግ የተሳሳተ መልዕክት ያስተላልፋል።
ቻይና የመካከለኛው ምስራቅን እያተራመሰው ያለው ጦርነት ወደ ቀጠናው ሊስፋፋ ይችላል የሚል ስጋቷንም ገልጻለች።
እስራኤል እና አጋሯ አሜሪካ ተኩስ አቁም ሀማስ መልሶ እንዲደራጅ ያደርገዋል በሚል ምክንያት አይቀበሉትም።
ባለፈው የፈረንጆቹ 2023 ጥር ወር ሀማስ የእስራኤልን ድንበር ጥሶ ከባድ ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ጦርነት አሁንም ቀጥሏል።
እስራኤል እየወሰደች ባለው የአጸፋ እርምጃ እስካሁን የተገደሉ ፍልስጤማውያን ቁጥር 29ሺ ማለፉን የጋዛ የጤና ሚኒስቴር ባለስልጣናት ተናግረዋል።