ተመድ በጸጥታው ምክር ቤት ድምጽን በድምጽ የመሻር መብት ያላቸውን ሀገራት ስልጣን ሊገድብ ነው
የድርጅቱ አባል ሀገራት በዚህ ጉዳይ ሊመክሩ መሆኑን አስታውቋል
ተመድ በጉዳዩ ላይ የሚመክረው ከአሜሪካ በቀረበለት ጥያቄ መሰረት ነው
ተመድ በጸጥታው ምክር ቤት ድምጽን በድምጽ የመሻር መብት ያላቸውን ሀገራት ስልጣን ሊገድብ መሆኑን አስታወቀ፡፡
ተመድ እንዳስታወቀው በጸጥታው ምክር ቤት አባል የሆኑ እና ደምጽን በድምጽ የመሻር መብት ያላቸውን ሀገራት ስልጣን መገደብ በሚቻልበት ዙሪያ ሊመክር መሆኑን አስታውቋል፡፡
የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ በዚህ ጉዳይ ላይ የሚመክረው ከአሜሪካ በቀረበለት ጥያቄ መሰረት ሲሆን ምክክሩ የሚካሄደው የተመድ አባል ሀገራት በተገኙበት መሆኑም ተገልጿል፡፡
አሜሪካ ቻይና፣ ሩሲያ፣ እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ ሲሆኑ አምስቱም አባል አገራት በማንኛውም ጉዳይ ላይ ውሳኔዎችን የመሻር መብት አላቸው፡፡
የተመድ ጠቅላላ ጉባኤም የነዚህን ሀገራት ድምጽን በድምጽ የመሻር ስልጣን በተወሰነ ደረጃ መገደብ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ዛሬ እንደሚመክር ይጠበቃል፡፡
ደምጽን በድምጽ የመሻር መብት ካላቸው አምስት ሀገራት መካከል አንዷ የሆነችው ሩሲያ በዩክሬን እያካሄደችው ያለው ጦርነት ለተመድ ጠቅላላ ጉባኤ መጠራት ምክንያት ሆኗልም ተብሏል፡፡
የዓለምን ጸጥታ ለመጠበቅ እንደተቋቋመ የሚነገረው የጸጥታው ምክር ቤትም የሩሲያን እና ዩክሬንን ጦርነት ሊያስቆም ባለመቻሉ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብት ያላት ሩሲያን ስልጣን ለመገደብ እንደሚወያይም ይጠበቃልም ተብሏል፡፡
የዛሬው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ አሜሪካንን ጨምሮ በ50 ሀገራት ድጋፍ የተጠራ ሲሆን ድምጽን በድምጽ የመሻር መብት ያላቸው አራቱ ቀሪ ሀገራት ድጋፍ እንዳልቸሩ የተመድ ሪፖርት አስታውቋል፡፡
ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የተመሰረተው የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት አምስት ቋሚ እና ሁለት ዓመቱ የሚቀያየሩ 10 ቋሚ ያልሆኑ ሀገራትን ይዟል፡፡