በቻይና በተማሪዎች መኖሪያ ክፍል በተከሰተ የእሳት አደጋ 13 ተማሪዎች ህይወታቸው አለፈ
ተማሪዎቹ የዘጠኝ አመት እድሜ ያላቸው እንደሆኑ ይገመታል
በእሳት አደጋው ህይወታቸው ያለፉት ተማሪዎች የሶስተኛ ክፍል ተማሪዎች መሆናቸው ተገልጿል
በቻይና በተማሪዎች መኖሪያ ክፍል በተከሰተ የእሳት አደጋ 13 ተማሪዎች ህይወታቸው አለፈ።
በቻይና ተማሪዎች በሚኖሩበት ክፍል ላይ በተቀሰቀሰ የእሳት አደጋ የ13 ተማሪዎች ህይወት ማለፉን ሮይተርስ ዘግቧል።
በማዕከላዊ ቻይና የተከሰተው እሳቱ 13 ተማሪዎች እንዲሞቱ እና ሌላ አንድ ሰው እንዲቆስል ምክንያት መሆኑን ዘገባው ጠቅሷል።
በእሳት አደጋው ህይወታቸው ያለፉት ተማሪዎች የሶስተኛ ክፍል ተማሪዎች መሆናቸው ተገልጿል።
ተማሪዎቹ የዘጠኝ አመት እድሜ ያላቸው እንደሆኑ ይገመታል።
ሮይተርስ የቻይናን ሴንትራል ቴሌቪዥን እና ሽንዋን ጠቅሶ እንደዘገበው የእሳት አደጋው በሄናን ግዛት በናንያንግ ከተማ አቅራቢያ በምትገኝ መንደር በትናንትናው እለት ነው የተከሰተው።
እሳቱ በፍጥነት መጥፋቱን እና የትምህርት ቤቱ ኃላፊ በቁጥጥር ስር መዋሉን ዘገባው ጠቅሷል።
ይንግሳይ ትምህርት ቤት መዋዕለ ህጻናትን እና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ያለው የግል አዳሪ ትምህርት ቤት ነው።
በዚህ ትምህርት ቤት የሚማሩ አብዛኞቹ ተማሪዎች ከገጠር አካባቢዎች የሚመጡ መሆናቸውም ተገልጿል።
ሲኤንኤን የሞቱ ተማሪዎች ቁጥር በትንሹ 20 እንደሆነ ዘግቧል።