ቻይና የአውሮፓ ህብረት በአጋርነት ላይ ያለውን አቋም 'ግልጽ' እንዲያደርግ አሳሰበች
የአውሮፓ ህብረትና ቻይና ሁሉን አቀፍ አጋርነት ከፍ ለማድረግ ቃል ገብተው ነበር
የአውሮፓ ህብረት መሪዎች በቻይና ላይ ጥገኝነት እንዲቀንስ ጥሪ አቅርበዋል
ቻይና የአውሮፓ ህብረት በአጋርነት ላይ ያለውን አቋም 'ግልጽ' እንዲያደርግ አሳሰበች።
የአውሮፓ ህብረት ስልታዊ አጋርነት ላይ ያለውን አቋም በስፋት "ማብራራት" እንዳለበት ተጠይቋል።
የቻይና ከፍተኛ ዲፕሎማት ዋንግ ዩ ለአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ኃላፊ ጆሴፕ ቦሬል ህብረቱ ከቤጂንግ ጋር ያለውን አቋም 'ግልጽ' እንዲያደርግ ጠይቀዋል።
ዲፕሎማቱ ይህን ያሉት የአውሮፓ ህብረት መሪዎች በቻይና ላይ ጥገኝነት እንዲቀንስ ጥሪ ካቀረቡ በኋላ ነው።
እ.አ.አ. በ2003 ይፋ የሆነው የአውሮፓ ህብረት-ቻይና ሁሉን አቀፍ ስልታዊ አጋርነት ከንግድ እና ኢንቨስትመንት ባሻገር ያለውን ግንኙነት ከፍ ለማድረግ ቃል ገብቷል።
ከ2019 ጀምሮ ግን የ27ቱ ሀገራቱ ህብረት ቻይናን "የኢኮኖሚ ተፎካካሪ" እና "የስርዓት ተቀናቃኝ" በማለት መድቧታል።
ቻይና እና የአውሮፓ ህብረት ግንኙነታቸውን ማጠናከር፣ የጋራ መተማመንን ማሳደግ እና ትብብርን ማጠናከር አለባቸው ያሉት ዲፕሎማቱ፤ ህብረቱ መመላለስን ማበረታታት ይቅርና "መወላወል" የለበትም ብለዋል።
ዋንግ በቻይና እና በአውሮፓ ህብረት መካከል ምንም አይነት መሰረታዊ የጥቅም ግጭት የለም ብለዋል።
ቦሬል በትዊተር ገጻቸው ከዋንግ ጋር የአውሮፓ ህብረት-ቻይና ግንኙነትን በመምራት ረገድ ያደረጉትን ንግግር "ገንቢ" እና "ጥልቅ" ሲሉ ገልጸዋል።