ፖለቲካ
ሰሜን ኮሪያ የብሊንከንን የቻይና ጉብኝት "የልመና ጉዞ" ስትል አጣጣለች
አሜሪካ "ጸረ ቻይና ቡድኖችን" በመፍጠር በቀጣናው ለሚፈጠረው ውጥረት ኃላፊነት አለባት ብለዋል
ብሊንከን ቻይና ሰሜን ኮሪያ የምታደርገውን የሚሳይል ተኩስ እንድታቆም እንድታግባባት ጠይቀዋል
ሰሜን ኮሪያ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን፣ አሜሪካ ከቻይና ጋር ያላትን ውጥረት ለማርገብ በማለም ያደረጉትን ጉብኝት "የልመና ጉዞ" ስትል ተችታለች።
ባይደን ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ ወሳኝ በተባለው ጉብኝት ወቅት ብሊንከን እና የቻይናው ፕሬዝደንት ሺ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ውጥረት ወደ ግጭት እንዳያመራ ግንኙነታቸውን ሰላማዊ ለማድረግ ተስማምተዋል።
ከስብሰባው በኋላ ብሊንከን እንደተናገሩት ቻይና ሰሜን ኮሪያ የምታደርገውን የሚሳይል ተኩስ እንድታቆም እንድታግባባት ጠይቀዋል።
ጆንግ ዮንግ ሃክ የተባሉት የሰሜን ኮሪያ የፖለቲካ ተንታኝ በኮሪያ ቴሌቪዥን ቀርበው እንደተናገሩት የብሊንከን የቻይና ጉብኝት በአሜሪካ ላይ ያልተጠበቀ ውድቀት ሊያስከትል የሚችለው ውጥረቱ እንደረግብ ለመለመን ነው ብለዋል።
ተንታኙ እንደገለጹት አሜሪካ በቻይና ላይ ያደረሰችው ትንኮሳ የፖሊሲ ውድቀት መሆኑን ያመኑት ዲፕሎማት ጉብኝት የልመና ጉዞ እንጅ ሌላ ሊባል አይችልም ብለዋል።
አሜሪካ "ጸረ ቻይና ቡድኖችን" በመፍጠር በቀጣናው ለሚፈጠረው ውጥረት ኃላፊነት አለባት ብለዋል።