ቻይና ሁለት ህጻትናን የገደሉ ጥንዶችን በሞት ቀጣች
ጥንዶቹ ህጻናቱን ከሚኖሩበት አፓርታማ 15ኛ ወለል ላይ በመስኮት ወርውረው ነው የገደሏቸው
ግድያ የተፈጸመባቸው ህጻናት የሁለት ዓመት ሴት እና የአንድ ዓመት ወንድ ልጅ ናቸው
ቻይና ሁለት ህጻናትን ከአፓርትመንት ህንጻ ላይ መስኮት ወርውረው የገደሉ ጥንዶች በሞት ቀጣች።
የልጆቹ አባት ዣንግ ቦ እና ዬ ቼንግቼን የተባለች ሴት በፈረንጆቹ በ2020 የሁለት ማመት ሴት እና የአንድ ዓመት ወንድ ልጅ በመግደል ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተዋል።
ዣንግ ቦ የተባለው የልጆቹ አባት ከዬ ቼንግቼን ከትዳሩ ውጪ የፍቅር ግንኙነት ጀመረ እና በኋላ ሚስቱን መፍታት ልጆቹን ለመግደል ማሴር መጀመሩም ተነግሯል።
የልጆች አባት የሆነው ዣንግ ቦ ስለ ቤተሰብ ሁኔታው እና ስለ ልጆቹ ሳይናገር ከዬ ቼንግቼን ጋር በድብቅ የፍቅር ግንኙነት የመጀመረ መሆኑ እና ፍቅረኛው እውነታውን ካወቀች በኋላም ግንኙነቷን መቀጠሏ በፍርድ ቤቱ ተነግሯል።
ዣንግ በፈረንጆቹ የካቲት 2020 ላይ ከልጆቹ እና ጋር ፍቺ ቢፈጽምም፤ አዲሷ ፍቅረኛ ዬ ሁለቱ ህጻት ዣንግን ለማግባት እንቅፋት እንደሆኑ እንዲሁም ለወደፊት ህይወታቸውም ሸክም አድርጋ መመልከቷ ነው የተገለጸው።
ይህንን ተከትሎም ዣንግ በልጆቹ ላይ ግድያ እንዲፈጽም ትወተውተው እንደነበረ በፍርድ ቤት የተገለጸ ሲሆን፤ አሟሟታቸውም ድንገተኛ አደጋ ለማስመሰል ማሴራቸውም ተመላክቷል።
በዚህ መሰረት ዣንት ልጆቹን በፈረንጆቹ 2020 ላይ ከሚኖሩበት የመኖሪያ አፓርታማ 15ኛ ፎቅ ላይ በመስኮት ወርውሮ መግደሉም በክስ መዝገቡ ተጠቅሷል።
የቻይና ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጥንዶቹ በህጻናቱ ላይ የፈጸሙት ግድያ “እጅግ ጭካኔ የተሞላበት” ሲል ገልጾታል።
ይህንን ተከትሎም ፍርድ ቤቱ በሁለቱ ጥንዶች ላይ የሞት ቅጣት የወሰነ ሲሆን፤ ቅጣቱም ባሳለፍነው ረቡዕ ተፈጸሚ መሆኑ እና ጥንዶቹ በደቡብ ምእራብ ቺንኮንግ ከተማ መገደላቸውም ተነግሯል።
የሞት ቅጣቱ በምን መልኩ ተፈጻ እንደተደረገ በግልጽ ያልተገለጸ ቢሆንም፤ በቻይና የሞት ፍርዶች በአብዛኛው የሚፈጸሙት በገዳይ መርፌ ወይም በተኩስ ቡድን መሆኑ ይነገራል።
የሞት ቅጣቱን ተከትሎም የልጆቹ እናት ቼን ሜሊን ትናንት ምሽት በሰጠችው አስተያየት፤ “ቤተሰቦቻችንን ለሶስት ዓመታት ያክል ሲያሰቃይ የነበረው ቅዠት አሁን አብቅቷል” ብላለች።