ሩሲያ ወታደሮቿን በሞት ቀጥታለች- ኃይት ኃውስ
አሜሪካ፣ ከሩሲያ ጋር ጦርነት እያካሄደች ላለችው ዩክሬን የገንዘብ እና የጦር መሳሪያ ድጋፍ ማድረጓን ቀጥላለች
ኃይት ኃውስ ሩሲያ በዩክሬኑ ጦርነት ግዳጅ አልቀበልም ያሉትን ወታደሮቿን በሞት መቅጣቷን የሚያሳይ መረጃ አሜሪካ እንዳላት አስታውቋል
ሩሲያ ትዕዛዝ አልበልም ያሉትን ወታደሮቿን በሞት መቅጣቷን ኃይት ኃውስ ገልጿል።
ኃይት ኃውስ በትናንትናው እለት እንደገለጸው ሩሲያ በዩክሬኑ ጦርነት ግዳጅ አልቀበልም ያሉትን ወታደሮቿን በሞት መቅጣቷን የሚያሳይ መረጃ አሜሪካ እንዳላት አስታውቋል።
"የሩሲያ ጦር ትዕዛዝ አልቀበልም ያሉ ወታደሮችን እንደገደለ መረጃው አለን" ሲሉ የኃይት ኃውስ ቃል አቀባይ ጆን ክርቢይ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።
ቃል አቀባዩ ከዚህ በተጨመሪም "የሩሲያ አዛዦች ከዩክሬን ለማፈግፈግ የሚሞክሩ ከሆነ ጠቅላላ የቡድኑ አባላትን እንደሚገድሉ ማስፈራራታቸውን የሚያሳይ መረጃ" እንደነበራቸው ተናግረዋል።
ሮይተርስ በዚህ ጉዳይ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴርን እና በአሜሪካ የሩሲያ ኢምባሲን ጠይቆ ምላሽ እንዳልሰጡት ዘግቧል።
በኃይት ኃውስ ክስ ላይ ምላሽ ለመስጠት ያልመረጡት በአሜሪካ የሩሲያ አምባሳደር አናቶሊ አንቶኖቭ በቅርቡ አሜሪካ ለዩክሬን ያቀረበችውን የ150 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ "ጸብ አጫሪ" ሲሉ ተቃውመውታል።
አሜሪካ፣ ከሩሲያ ጋር ጦርነት እያካሄደች ላለችው ዩክሬን የገንዘብ እና የጦር መሳሪያ ድጋፍ ማድረጓን ቀጥላለች።
ኔቶ ወደ ቀድሞ የሶቬት ሀገራት መስፋፋት የደህንነት ስጋት እንደሚፈጥርባት በመግለጽ ነበር ሩሲያ በዩክሬን ላይ እስካሁን ያልተቋጨውን ልዩ ያለችውን ወታደራዊ ዘመቻ የከፈተችው።