በፔሎሲ ጉብኝት የተቆጣችው ቻይና ወደ ታይዋን ሚሳኤል አስወነጨፈች
ቻይና በታይዋን ዙሪያ እስከ ቀጣዩ እሁድ የሚቆይ ወታደራዊ ልምምድ በማድረግ ላይ ትገኛለች
በታይዋን መዲና ቴፒ ሰላም ቢሆንም ዜጎች በሁኔታው ጭንቀት ውስጥ መውደቃቸው ተገልጿል
ቻይና ዶንግፋንግ የተሰኙ ሚሳኤሎችን ወደ ታይዋን ኣስወነጨፈች።
የአሜሪካ ምክር ቤት አፈጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ ታይዋንን ጨምሮ አምስት የእስያ ሀገራትን መጎብኘታቸውን ተከትሎ በሩቅ ምስራቅ ውጥረት እንደነገሰ ነው።
አፈ ጉባኤዋ ከትናንት በስቲያ ታይዋንን ጎብኝተው ወደ ሌላ ሀገር ያቀኑ ሲሆን ድርጊቱ ቻይናን እንዳስቆጣ የዓለም ብዙሀን መገናኛዎች ዘግበዋል።
ይሄንን ተከትሎም ቻይና በታይዋን ባህር ዙሪያ እስከ ቀጣዩ እሁድ ድረስ የሚቆይ ወታደራዊ ልምምድ በማድረግ ላይ ትገኛለች ።
በዛሬው የወታደራዊ ልምምድም የአየር፣የባህር እና የየብስ ጦርነት ልምምድ ሜድረጓን ሮይተርስ ዘግቧል።
እንደ ዘገባው ከሆነ ቻይና በታይዋን 20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በስድስት አቅጣጫ የጦርነት ልምምዱ እየተካሄደ ይገኛል ተብሏል።
ዶንግ ፋንግ የተሰኘው የቻይና የረጅም እና አጭር ርቀት ባልስቲክ ሚሳኤሎች ወደ ታይዋን ባህር የትተኮሱ ሲሆን እስካሁን የደረሰ ጉዳት እንደሌለ ተገልጿል።
በታይዋን ስድስት አቅጣጫዎች ምንም አይነት የባህር እና አየር ላይ ትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንዳይኖር ቻይና አስቀድማ አስጠንቅቃለች።
ታይዋን የቻይና ድርጊት የጦርነት ትንኮሳ መሆኑን አስታውቃ እስከ እሁድ የሚቆየውን የጦር ልምምድ እንደማትታገሰው ገልጻለች።የታይዋን ፕሬዝዳንት ሆይ እንግዲህ ዌን በተለይ የቡድን ሰባት ሀገራትን ለታይዋን ላሳዩት ድጋፍ አመስግነዋል።
ፕሬዝዳንቷ ይሄንን ያሉት የቡድን ሰባት ሀገራት ቻይና ከታይዋን ጋር ያላትን ጉዳይ በሰላማዊ መንገድ እንድትፈታ መናገራቸውን ተከትሎ ነው።
ቻይና እና ታይዋን በፈረንጆቹ 1996 ላይ የተካረረ ግንኙነት የነበራቸው ሲሆን ሁለቱም አካላት ግጭትን ላለማባባስ በሚል አይነኬ የተባለ ቦታ በመካከላቸው በመተው ሰላም ያወረዱ ቢሆንም ይህ አይነኬ የባህር ስፍራ በቻይና መያዙ ዘገባዎች ጠቅሰዋል።