አሜሪካ በፓስፊክ ውቅያኖስ ያላትን ጦር ወደ ታይዋን አስጠግታለች
የአሜሪካ አፈ ጉባኤ ናንሲ ሌሎሲ ታይዋንን ጨምሮ አምስት የእስያ ሀገራትን ጉብኝት መጀመራቸውን ተከትሎ ዓለም አይኑ ታይዋን ላይ አርፏል።
ቻይና በአሜሪካ ፖለቲካ ሶስተኛው የስልጣን ባለቤት እየሆኑት ናንሲ ፔሎሲ ታይዋንን ከጎበኙ እርምጃ እወስዳለሁ ማለቷን ተከትሎ በሩቅ ምስራቅ ውጥረት ነግሷል።
አፈ ጉባኤ ናንሲ የሲንጋፖር ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደ ታይዋን እንደሚገቡ የታይዋን መንግስታዊ እና የግል ብዙሀን መገናኛዎች በመዘገብ ላይ ናቸው።
ይሄንን ተከትሎም አስቀድማ ናንሲ ፔሎሲ ታይዋንን ከጎበኙ እርምጃ እወስዳለሁ ያለችው ቻይና የአየር እና የባህር ሀይል ጦሯን ወደ ታይዋን አቅርባለች።
የታይዋን መንግስትም ለሶስት ቀናት የሚቆይ የአደጋ መቋቋም ሀይሏን እንዳዘጋጀች አስታውቃለች።
ይህ የአደጋ መቋቋም ዝግጁነት ሀይል ከዛሬ ጀምሮ እስከ ቀጣዩ ሀሙስ ድረስ እንደሚቆይ ተገልጿል።
በቻይናው ግሎባል ታይምስ ላይ ትንታኔዎችን በመጻፍ የሚታወቀው ሁ ጂያን የአሜሪካ ወታደራዊ አውሮፕላኖች ናንሲ ፔሎሲን አጅበው ወደ ታይዋን ለማስገባት ካሰቡ ይህ አሜሪካ በግልጽ በቻይና ላይ ወረራ እንደፈጸመች ይቆጠራል። የቻይና ጦርም አውሮፕላኑን መምታት እንዳለበት በትዊተር ገጹ አስፍሯል።
የአሜሪካ እና ቻይና የጦር አውሮፕላኖች እና የባህር ላይ ወታደሮቻቸውን ወደ ታይዋን አቅርበዋል።