ታይዋን፤ ቻይና ልትወረኝ ትችላለች ስትል ስጋቷን ገልጻለች
የታይዋንን የአየር ክልል ጥሰው ከገቡ የየቻይና ጦር አውሮፕላኖች መካከል ቦንብ ጣይና የውጊያ ሂልኮፕተሮች ይገኛሉ
ቻይና ለሁለተኛ ጊዜ 18 የጦር አውሮፕላኖችን ወደ ታይዋን ላከች
ታይዋን የግዛቴ አንድ አካል ናት የምትለው ቻይና 18 ተዋጊ አና ቦንብ ጣይ አውሮፕላኖች መላኳ ተገልጿል።
የታይዋን አየር መከላከያ ክልል እንደተናገረው የቻይና ተዋጊ አውሮፕላኖች የታይዋንን የአየር ክልል ጥሰው እንደገቡ አስታውቋል።
ቻይና የታይዋንን የአየር ክልል ጥሳ ስትገባ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው የተባለ ሲሆን ታይዋን የዩክሬን እጣ ሊደርሳት እንደሚችል ስጋት እንደገባት ገልጻለች።
አሜሪካንን ጨምሮ የዓለም ሀገራት አንድ ቻይና እንዲያከብር በማሳሰብ ላይ ብትሆንም ምዕራባዊያን ሀገራት ግን ታይዋን የቻይና አንድ አካል አይደለችም ሲሉ ይደመጣሉ።
ቻይና በአንጻሩ ባለፉት ሁለት ዓመታት ታይዋን የግዛቷ አንድ አካል መሆኗን ገልጻ የውጊያ አውሮፕላኖችም ወደ ታይዋን ቢገቡ ወደራሳቸው ግዛት ገቡ እንጂ የማንንም የአየር ክልል አለመጣሷን ከዚህ በፊት አሳውቃለች።
ታይዋን ባቀረበችው የዛሬው የአየር ክልሌ ተጣሰ ክስ ዙሪያ እስካሁን ምላሽ ያልሰጠችው ቻይና ሉዓላዊነቷን በሚዳፈር ሀገርም ይሁን ተቋም ላይ ከባድ እርምጃ እንደምትወስድ ከዚህ በፊት ማስጠንቀቋ ይታወሳል።
የዓለም ትኩረት ሁሉ በሩሲያ-ዩክሬን ላይ በመሆኑ ቻይና ታይዋንን ልትወር ትችላለች የሚል ስጋት መኖሩን የታይዋን ባለስልጣናት ተናግረዋል።
ባሳለፍነው ጥር ወር የቻይና ተዋጊ አውሮፕላኖች የታይዋንን የአየር ክልል ጥሰው እንደገቡ ዓለም አቀፉ የአየር መከላከያ ልየታ ቀጠና ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።
ከቀናት በፊት አውሮፓን የጎበኙት የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ በእንግሊዟ መዲና ለንደን ላይ ባሰሙት ንግግራቸው ዓለም ለሩቅ ምስራቅ ትኩረት ካላደረገ የምስራቅ አውሮፓው ክስተት በምስራቅ እስያም ሊደገም ይችላል ብለዋል።
የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባሳለፍነው ዓርብ ባወጣው መግለጫ ጃፓን ከጸብ አጫሪነቷ እንድትታቀብ አስጠንቅቋል።
ሚኒስቴሩ አክሎም ጃፓን በእስያ እና በዓለም ሰላም እንዲመጣ ከፈለገች በዓለማችን ሀያላን ሀገራት መካከል ገብታ ጸብ ከምታጭር ሀገራትን ወደ ጦርነት እንዲገቡ ከመተንኮስ ትታቀብ ሲልም አሳስቧል።