ከቻይና የወረራ ስጋት ያለባት ታይዋን ጦርነት ለመቋቋም የሚያስችል መመሪያ አዘጋጀች
የታይዋን ፕሬዝዳንት ሀገሪቱን ለመከላከል ጦር የማዘመን ስር መኖሩን አስታውቀዋል
የታይዋን መከላከያ ቻይና ጦርነት ብትከፍት ዜጎች እንዴት ከጦርነቱ መዳን ይችላሉ የሚል መመሪያ ይፋ አድርጓል
ሩሲያ በዩክሬን እያካሄደች ያለቸው ጦርነት ታይዋን በቻይና የሚደርስባትን ጫና እንዴት ልትቋቋመው ትችላች የሚል ትኩረት በሳበበት ወቅት፣ የታይዋን መከላከያ ቻይና ጦርነት ብትከፍት ዜጎች እንዴት ከጦርነቱ መዳን ይችላሉ የሚል መመሪያ ይፋ አድርጓል፡፡
ቻይና ታይዋንን በቁጥጥሯ ስር ለማድረግ ኃይል እንደማትጠቀም አልገለጸችም፤ ባለፉት ሁለት አመታት በታይዋን ድንበት አቅራቢያ ወታደራዊ ልምምድ በማድረግ ጫና እየፈጠረች መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
መመሪያው በስማርት ስልክ አማካኝነት እንዴት ከቦንብ ጥቃት የሚያድን መጠለያ፤የውሃ እና የምግብ አቅርቦት እና የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ ቁሳቁስ ማግኘት እንደሚቻል ይዘረዝራል፡፡
ታይዋን ይህን መመሪያ ያዘጋጀችው ሩሲያ በዩክሬን የከፈተችውን ልዩ ወታደራዊ መነሻ በማድረግ መሆኑን እና ይህም የታይዋን ዝግጁነት ከፍ ያደርገዋል ተብሏል፡፡
በሚኒስቴሩ የሁሉን አቀፍ መከላከል ባለስልጣን የሆኑት ሊዩ ታይ ይ እንደገለጹት ዜጎች ወታራዊ ቀውስ እና ሌሎች አደጋዎች ቢከሰቱ ምንማድረግ እንዳለባቸው መረጃ እንሰጣለን ብለዋል፡፡
መመሪያው ዜጎችን ከጥቃት ያድናል ያሉት ባለስልጣኑ ወታደራዊ ጥቃትን እንዴት ማምለጥ እንደሚቻል ስእላዊ መግለጫዎች ተካተውበታል ብለዋል፡፡
ታይዋን ከቻይና የሚሰነዘር አይቀሬ ጥቃት አለ ብሏ ባትገልጽም፣ ሩሲያ በዩክሬን “ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ” ከጀመረች በኋላ ጥንቃቄዋን ከፍ እድርጋለች፡፡
የታይዋን ፕሬዝዳንት ሀገሪቱን ለመከላከል ጦር የማዘመን ስር መኖሩን አስታውቀዋል፡፡