የቻይና አየር ሃይል 150 የጦር አውሮፕላኖችን በመጠቀም ለአራት ተከታታይ ቀናት የታይዋንን የአየር ክልል ጥሶ ሲንቀሳቀስ ነበር
በቻይናና በታይዋን መካከል ለሳምንታት የዘለቀውን ውጥረት ተከትሎ የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጅንፒንግ ታይዋንን ከቻይና ጋር ለማዋሃድ ዝተዋል፤ፕሬዝዳንቱ ለማዋሃድ ኃይል መጠቀም ስለማሰባቸው አልተናገሩም፡፡
በዲሞክራሲያዊ ስርአት የምትተዳደረው ታይዋን የቻይናን ሉአላዊነት እንድታከብር ጫና እያደረባት ሲሆን ታይፒ ግን ነጻነቷን ለማስጠበቅ እንደምትሰራና ማንኛውንም ጉዳይ የሚወስነው የታይዋን ህዝብ መሆኑን እየገለጸች ነው፡፡ ዢ ጅንፒንግ በቻይና ታሪካዊ የሆነ ተገንጣይነትን የመቃወም ባህል መኖሩ ተናግረዋል፡፡
የመጨረሻው የኢምፔሪያል ዳይናስቲ በፈረንጆቹ 1911እንዲወርድ ምክንያት የሆነው ሪቮሉሽን ክብረበአል ላይ ፕሬዝዳንቱ እንደተናገሩት የታይዋን የመገንጠል እንቅስቃሴ ከታይዋን ጋር ውህደት ለመፈጸም እንቅፋት ይሆናል፤ጉዳይ ለብሄራዊ እድገት አደገኛ ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡
ታይዋን ከቻይና ጋር የማዋሃድ ታሪካዊ ኃላፊነት መጠናቀቅ አለበት፤በእርግጠኝነት ይጠናቀቃልም ብለዋል ፕሬዝዳንት ዢ፡፡ የቻይና አየር ሃይል በ150 የጦር አውሮፕላኖች በመጠቀም ለአራት ተከታታይ ቀናት የታይዋንን የአየር ክልል ገብቷል፤ ጉዳዩ ግን አሁን ቆሟል፡፡
ነገርግን ታይዋን ታይና ነጻ ሀገር ነች፤የመዋሃድ ጥያቄውን አትቀበለውም፡፡
ቻይና በታይዋን ጉዳይ ከአሜሪካ ጋር ጭምር በተደጋጋሚ ግጭት ውስጥ ስትገባ ይታያል፤አሜሪካ ቻይና የታይዋንን ነጻነት እንድታከብር ስትጠይቅ፤ቻይና በአንጻሩ ታይዋንን የግዛቷ አካል አድርጋ ትመለከታታለች፡፡ ቻይና ከታይዋን ጋር ትብብር የሚያደጉ ሀገራትን አጥብቃ ትቃወማለች፡፡