ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ቻይና ለጋራ ጥቅም ከአሜሪካ ጋር ለመስራት ፈቃደኛ ነች አሉ
የፔሎሲ የታይዋን ጉብኝት ተከትሎ የሁለቱም ኃያላን ሀገራት ግንኙነት ጥሩ የሚባል እንዳልሆነ ይታወቃል
የጆ ባይደን አስተዳደር ዋሽንግተን ከቤጂንግ ጋር ያሏት የግንኙነት መስመሮችን ክፍት እንደሚያደረግ አስታውቋል
የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ቻይና ለጋራ ጥቅም ከአሜሪካ ጋር ለመስራት ፍቃደኛ ናት ማለታቸው የቻይና መንግስት ቴሌቪዥን ዘግቧል፡፡
ፕሬዝዳንቱ በትናንትናው እለት በተዘጋጀውና በአሜሪካ - ቻይና ግንኙነት ዙሪያ ትኩረት የሚያደረገው የጋራ ብሔራዊ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ እንደተናገሩት ከሆነ ሁለቱም ኃያላን ሀገራት ግንኙነታቸውንና ትብብር በማጠናከር ለዓለምና መረጋጋት ትልቅ ሚና መጫወት አለባቸው ብለዋል፡፡
ዢ ይህን መልዕክት ያስተላለፉት በቅርቡ በኢንዶኔዥያ በሚካሄደው ቡድን-20 ስብሰባ ከፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ሊያደርጉት ከሚችሉት ውይይት በፊት መሆኑ ነው፡፡
ጆ ባይደን በበኩላቸው “አሜሪካ ከቻይና ጋር ግጭ አትፈልግም” ሲሉ ተደምጠዋል።
ፕሬዝዳንት ዢ ለሶስተኛ ጊዜ የቻይና መሪ ሆነው መመረጣቸውን ተከትሎ ዋሽንግተን ከቤጂንግ ጋር ያሏት የግንኙነት መስመሮችን ክፍት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አጽንዖት ሰጥተውም ተናግራል ፕሬዝዳንቱ።
የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፔሎሲ የታይዋን ጉብኝት ተከትሎ የሁለቱም ሀገራት ግንኙነት ጥሩ የሚባል እንዳልሆነና በበርካታ ዛቻዎች የታጀበ መሆኑ ይታወቃል፡፡
በተለይም በፔሎሲ ጉብኝት ምክንያት የተበሳጨችው ቻይና እና ከአሜሪካ ጋር ወታደራዊ ትብብርን ጨምሮ በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያም ንግግርና ውይይት የነበራት ቢሆንም ሁሉንም ማቋረጧ የሚታወስ ነው፡፡
ከዚህ ባለፈም የፕሬዝዳንት ዢ ሺን ፒንግ አስተዳደር፤ ሀገሪቱ ከአሜሪካ ጋር የነበራትን የድንበር አልባ ወንጀል መከላከል፣ ስደተኞችን የማጓጓዝ፣ አደገኛ ዕጽ ዝውውር መከላከል እና ሌሎች ስምንት የትብብር መስኮችን ማቋረጡን ገልጾ ነበር፡፡
አሜሪካ በበኩሏ የቻይና ድርጊት ተገቢ እንዳለሆነ ስትሞግት ቆይታለች፡፡
ያም ሆኖ የሁለቱም ኃያላን ሀገራት መሪዎች አሁን ላይ አዲስ ተረክ ይዘው መምጣታቸው የሀገራቱ ግንኙነት ወደ ተሻለ ደረጃ ያደርሷል ተብሏል፡፡
በተለይም ሀገራቱም ሀገራት ከተባበሩ ለዓለም ሰላም የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደሆነ ይታመናል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) ዋና ኃላፊ ከአሜሪካ-ቻይና ትብብር ውጭ የዓለም አቀፍ ቁልፍ ጉዳዮችን ለመፍታት የሚደረግ 'ምንም መንገድ የለም' ብለው እንደሚያምኑ በቅርቡ መናገራቸው አይዘነጋም፡፡