ቻይና ሌላውን የመካከለኛው ምስራቅ የዲፕሎማሲያዊ ችግር ለመፍታት እያማተረች ነው ተባለ
ቤጂንግ የተወሳሰበውን የኢራን-ሳዑዲ አረቢያን አለመግባበሰት "በተሳካ ሁኔታ አሸማግያለሁ" ብላለች
ቻይና እስራኤልን እና ፍልስጤምን ለማስታረቅ አይኗን ጥላለች
ቻይና በመካከለኛው ምስራቅ ያስመዘገበችውን ዲፕሎማሲያዊ ስኬት ለማሳደግ መወጠኗ ተነግሯል።
ቤጂንግ በእስራኤል እና ፍልስጤም ለማሸማገል እያማተረች መሆኑም ነው የተቸለጸው።
በሰኔ ወር አጋማሽ ላይ የፍልስጤም ፕሬዝዳንት ማህሙድ አባስ ቤጂንግ የጎበኙት ሲሆን፤ በቻይና መሪ ዢ ጂንፒንግ ደማቅ አቀባበልም ተደርጎላቸዋል።
ሁለቱም ወገኖች ስልታዊዊ አጋርነት ላይ የተፈራረሙ ሲሆን፤ ይህም ለሁለቱዮሽ ግንኙነቱ ትልቅ እርምጃ ነው ተብሏል።
ቻይና እስራኤልን እና ፍልስጤምን ለማስታረቅ የምታደርገው ጥረት፤ ቤጂንግ ከዚህ ቀደም የተወሳሰበውን የኢራን-ሳዑዲ አረቢያን ግንኙነት "በተሳካ ሁኔታ" አቀላጠፍኩ ካለች በኋላ የተጀመረ ነው።
ሀገሪቱ ከምዕራባውያን ጽንሰ-ሀሳቦች ሌላ አማራጭን ይፋ በማድረግ ለዓለም ሰላምና ደህንነት እንደምትሰራ ገልጻለች።
የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ኪን ጋንግ በእስራኤል እና በፍልስጤም መካከል የግጭት አፈታት ዋና ዋና መርሆዎችን አስታውቀዋል።
ለምሳሌ ሲሉም ፍልስጤምን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ውስጥ ሙሉ አባልነትን መደገፍ እና "የሁለት-ግዛት መፍትሄ" ጽንሰ-ሀሳብን አቅርበዋል።
ሆኖም ይህን ማሳካት ቀርቶ ፊት ለፊት ማቀራረቡ ከባድ እንደሚሆን ተገምቷል።
የፍልስጤም ባለስልጣን የታቀደውን ፕሮግራም ሙሉ በሙሉ ቢደግፉም፤ እስራኤል ግን ተቃወማለች።
በእስራኤል ውስጥ "የሁለት-ግዛት መፍትሄ" የኃይል ሚዛኑ በመቀየሩ ቅቡልነት አይኖረውም ተብሏል።
ቻይና የፍልስጤም ግዛትን እውቅና ከሰጠችበት ጊዜ አንስቶ የፍልስጤም ጉዳይ ደጋፊ ናት።