ፖለቲካ
የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ቻይና የዓለም "የጸጥታና የብልጽግና" ስጋት ነች አሉ
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን የተናገሩት ከቡድን ሰባት ሀገራት ስብሰባ በኋላ ነው
ሱናክ እንዳሉት እንግሊዝ እና ሌሎች የቡድን ሰባት አባል ሀገራት በቻይና የተደቀነውን ስጋት ለመቀነስ መስራት አለባቸው
የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ሪቺ ሱናክ ቻይና የዓለም የጸጥታና የብልጽግና ስጋት ነች ሲሉ ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን የተናገሩት ከቡድን ሰባት ሀገራት ስብሰባ በኋላ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት መግለጫ "ቻይና የዘመናችን የጸጥታና የብልጽግና ስጋት ነች። አሃዳዊነታቸው በሀገር ውስጥ እና በውጭ የተረጋገጠ ነው።" ብለዋል።
ሱናክ እንዳሉት እንግሊዝ እና ሌሎች የቡድን ሰባት አባል ሀገራት በቻይና የተደቀነውን ስጋት ለመቀነስ መስራት አለባቸው።
ባለፈው ሳምንት የቀድሞዋ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዝ ትረስ ታይዋንን በመጎብኘት፣ ምዕራባውያን "ቻይናን መለማመጥ" የለባቸውም ካሉት ታይዋንን በፈረንጆቹ 1990ዎቹ ከጎበኙት ማርጋሬት ታቸር ወዲህ ታዋቂ ፖለቲከኛ ናቸው።
ቻይና በታይዋን ዙሪያ ያሳየችው አቋም ውጥረት እንዲነግስ አድርጓል። ቻይና ታይዋንን የግዛቷ አካል ለማድረግ የኃይል አማራጭ እንደማትጠቀም አለመግለጿ በምዕራባውያን ተቀባይነት የለውም።