ቻይና በሶላር ኢነርጂ ቀዳሚ ሀገር ሆነች
መንግስት ስኬታማ እቅድ ስላስቀመጠ የቻይና የሶላር ኃይል በሚቀጥሉት አመታ ከፍተኛ እድገት ያስመዘግባል ተብሏል
በአሁኑ ወቅት ቻይና እያመነጨት ያለችው 500 ጊጋዋት የሶላር ኃይል የአለምን 40 በመቶ በመሸፈን ቀዳሚ አድርጓታል
ቻይና በሶላር ኢነርጂ ቀዳሚ ሀገር ሆነች።
በ2026 1ቴራዋት ኃይል የምታመነጨው ቻይና በሶላር ኃይል ቀዳሚ ሆናለች።
መንግስት ስኬታማ እቅድ ስላስቀመጠ የቻይና የሶላር ኃይል በሚቀጥሉት አመታ ከፍተኛ እድገት ያስመዘግባል ተብሏል። ቻይና አሁን ላይ ከሶላር ኃይል 500 ጊጋዋት የማመንጨት አቅም አላት፤ እዚህ አቅም ላይ ለመድረስ 13 አመታትን ፈጅቶባታል።
ነገርግን አሁን ያላት አቅም በእጥፍ በመጨመር በሶስት ተጨማሪ አመታት ውስጥ ወደ 1 ቴራዋት ይደርሳል።
የራይስታድ ኢነርጂ ሞዴል እንደሚያመለክተው በ2026 የቻይና የሶላር ኃይል 1000 ጊጋዋት እንደሚደርስ ተገምቷል። በ2023 ቻይና ከሶላር ያገኘችው አዲስ ኃይል 150 ጊጋ ዋት ሲሆን ይህም ከ2022 ከተመረተው 87 ጊጋዋት እጥፍ ገደማ ነው።
የቻይና ጠቅላላ የሶላር ኃይል በ2026 አንድ ቴራ ዋት ከመድረሱ በፊት፣ በ2024 700 ጊጋዋት እና በ2025 ደግሞ ወደ 900 ጊጋዋት ከፍ እንደሚል ይገመታል።
በአሁኑ ወቅት ቻይና እያመነጨት ያለችው 500 ጊጋዋት የሶላር ኃይል የአለምን 40 በመቶ በመሸፈን ቀዳሚ አድርጓታል።በአሁኑ ወቅት ቻይና እያመነጨት ያለችው 500 ጊጋዋት የሶላር ኃይል የአለምን 40 በመቶ በመሸፈን ቀዳሚ አድርጓታል