ክፍት ቤቶችን 1.4 ቢሊዮን የቻይና ህዝብ እንኳን አይሞላቸውም ሲሉ የቀድሞ ባለስልጣን ተናገሩ
ኬንግ በሀገሪቱ የተረጋጋ ነው በሚባለው ዘረፍ ላይ መንግስት ከሚያራምደው ትርክ የሚቃረን ትችት በህዝባዊ ስብሰባ ላይ ሰንዝረዋል
በሀገሪቱ ቀውስ ውስጥ በገባው የሪልኢስቴት ገበያ ላይ ያልተለመደ ትችት ያቀረቡት እኝህ ባለስልጣን እንደገለጹት የተበታተኑትን ክፍት ቤቶች ለመሙላት ሁሉም የቻይና ህዝብ ብቻ በቂ አይደለም
አንድ የቀድሞ የቻይና ባለስልጣን በቻይና ያሉትን ክፍት ቤቶች የቻይና 1.4 ቢሊዮን ህዝብ እንኳን አይሞላቸውም ሲሉ ተናግረዋል።
በሀገሪቱ ቀውስ ውስጥ በገባው የሪልኢስቴት ገበያ ላይ ያልተለመደ ትችት ያቀረቡት እኝህ ባለስልጣን እንደገለጹት የተበታተኑትን ክፍት ቤቶች ለመሙላት ሁሉም የቻይና ህዝብ ብቻ በቂ አይደለም።
በቻይና የኢኮኖሚ ምሰሶ የነበረው የሪልኢስቴት ዘርፍ በፈረንጆቹ 2021 ግዙፉ የሪልኢስቴት ኩባንያ ኤቨርግራንዴ ብድሩን መክፈል ባለመቻሉ ምክንያት ዘርፉ ተቀዛቅዟል።
ትልቅ ስም ያላቸው እንደ ካንትሪ ጋርደን ሆልዲንግስ ያሉት አልሚዎች በመንገዳገዳቸው ምክንያት ቤት ገዥዎች ተስፋ እንዲቆርጡ አድርጓቸዋል።
እስከ ባለፈው ነሐሴ ድረስ ያልተሸጡ ቤቶች ሰባት ቢሊዮን ፊት ጠቅላላ ስፋት እንዳላቸው ሮይተርስ ዘግቧል።
ይህ ማለት በአማካኝ አንድ ቤት ሊኖረው በሚችል አማካኝ ስፋት ሲሰላ 8.2 ሚሊዮን ቤቶች ይሆናሉ። እንደዘገባው ከሆነ ቁጥሩ የተሸጡ በርካታ የመኖሪያ ቤት ፕሮጀክቶችን እና በገንዘብ እጥረት ምክንያት ያልተጠናቀቁትን አያካትትም።
"አሁን ስንት ክፍት ቤቶች አሉ። ሁሉም ባለሙያዎች የተለያዩ ቁጥሮች ያስቀመጡ ሲሆኑ ጫፍ የወጡት ለሶስት ቢሊዮን ህዝብ የሚበቁ ክፍት ቤቶች አሉ ብለው ያምናሉ" ሲሉ የተናገሩት የቀድሞው የስታቲስቲክስ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ሂ ኬንግ ናቸው።
ኪንግ ያ ግምት ሊበዛ ይችላል፣ ነገርግን 1.4 ቢሊዮን ህዝብ ሊሞላው አይችልም ብለዋል። ኬንግ በሀገሪቱ የተረጋጋ ነው በሚባለው ዘረፍ ላይ መንግስት ከሚያራምደው ትርክት የሚቃረን ትችት በህዝባዊ ስብሰባ ላይ አሰምተዋል።