አውሮፕላኑ የእሳት አደጋን ለመከላከልና በባህርተኞች ላይ አደጋ ሲደርስባቸው ለመታደግ ያገለግላል
በቻይና የተሰራውና በውኃ ላይም በጓዝ የሚችለው ግዝፍ አውሮፕላን የተሳካ የመጀመሪያ የሙከራ በረራ ማድረጉ ተገለጸ።
በቻይና አቪዬሽን ኢንደስትሪ ኮርፖሬሽን የተሰራው አውሮፕላኑ በአየር ላይ መብረር እንዲሁም በውኃ ላይም መጓዝ እንደሚችል ተነግሯል።
አውሮፕላኑ አራት ሞተሮች የተገጠሙለት መሆኑንም የሲ.ጂ.ቲ.ኤን ዘገባ ያመለክታል።
ታዲያ ባሳለፍነው ሃሙስ በአውሮፕላኑ የበረራ ሙከራ የተደረገ ሲሆን፤ የመጀመሪያ ሙከራውም የተሳካ መሆኑንም ኩባያው አስታውቋል።
በሙከራው ወቅት አራቱም የአውሮፕላኑ ሞተሮች ማለትም ሞተር 1፣ 2፣ 3 እና 4 ሙሉ በሙሉ በአግባቡ መስራቸውን የሚከውኑ መሆኑ የተረጋገጠ ሲሆን፤ ሁሉም አውሮፕላኑ ሲስተሞችም ትክክል መሆናቸው ተረጋግጧል ነው ተባለው።
“ኩነሎንግ” የሚል መጠሪያ የተሰጠው አውሮፕላኑ በተለይም ለአደጋ መከላከል እና ለነብስ አድን ስራዎች በርካታ ጠቀሜታዎችን የሚሰጥ መሆኑ ተነግሮለታል።
አውሮፕላኑ በተለይም የእሳት አደጋን ለመከላከል፣ ባህርተኞችን በውሃ ላይ እያሉ አደጋ ሲያጋጥማቸው ፈጥኖ ለመታደግ እና ሌሎችም ወሳኝ ለሆኑ የአደጋ መከላከል ስራዎች ላይ አጋዥ እንደሚሆን ታምኖበታል።
የመጀመሪያው AG600-1003 አውሮፕላን ምርት ባሳለፍነው ህዳር ወር ተጠናቀቀ ሲሆን፤ በያዝነው የፈረንጆቹ 2022 ሁለት ተጨማሪ ተመሳሳይ አውሮፕኖች እንደሚመረቱም ተነግሯል።