አሜሪካ የሀውቲን የጸረ-መርከብ ሚሳይል መምታቷን አስታወቀች
ሀውቲዎች በቀይ ባህር ላይ ጥቃት የሚሰነዝሩት ከእስራኤል ጋር እየተዋጋ ላለው ሀማስ አጋርነት ለማሳየት እንደሆነ መግለጻቸው ይታወሳል
የእስራኤል እና ሀማስ ግጭት መቀስቀሱን ተከትሎ የተከሰተው የቀይ ባህር ውጥረት እየጨመረ መጥቷል
አሜሪካ የሀውቲን የጸረ-መርከብ ሚሳይል መምታቷን አስታወቀች።
አሜሪካ ጦር በትናትናው እለት በየመን በሀውቲ ይዞታ ስር ባለ ቦታ በጸረ-መርከብ ሚሳይል ላይ አዲስ ጥቃት ፈጽማለች።
በቀይ ባህር ስትንቀሳቀስ የነበረች የግሪክ መርከብ ጥቃት እንደደረሰባት ሮይተርስ ዘግቧል።
በኢራን ይደገፋል የሚባለው የሀውቲ ታጣቂ ቡድን ከባለፈው ህዳር ወር ጀምሮ በቀይ ባህር በሚንቀሳቀሱ መርከቦች ላይ የሚያደርሰው ጥቃት በብዙ ኩባንያዎች ላይ ተጽዕኖ አሳድሯል።
ሀውቲዎች በቀይ ባህር ላይ ጥቃት የሚሰነዝሩት ከእስራኤል ጋር እየተዋጋ ላለው ሀማስ አጋርነት ለማሳየት እንደሆነ መግለጻቸው ይታወሳል።
በቀይ ባህር የሚንቀሳቀሱ መርከቦችን ደህንነት አስጠብቃለሁ የምትለው አሜሪካ፣ በርካታ ሀገራት ያካተተ ግበረ ኃይል አቋቁማ ወደ ስራ ገብታለች።
በቅርቡ አሜሪካ እና ዩኬ በየመን ግዛት ውስጥ በሀውቲ ቡድን ይዞታ ላይ ጥቃት አድርሰዋል፤ የሀውቲ ታጣቂዎችም ለደረሰው ጥቃት ምላሽ እንደሚሰጡ መዛታቸው የሚታወስ ነው።
ሀውቲዎች ገንዘብ እና የጦር መሳሪያ እንዳይደርሳቸው፣ የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን አስተዳደር በድጋሚ የሽብር ቡድን ዝርዝር ውስጥ ሊከታቸው እንደሚችል ሮይተርስ ዘግቧል።
የእስራኤል እና ሀማስ ግጭት መቀስቀሱን ተከትሎ የተከሰተው የቀይ ባህር ውጥረት እየጨመረ መጥቷል።