የሀውቲ ታጣቂዎች ወደ እስራኤል የሚያቀኑ ሁሉንም መርከቦች ኢላማ እንደሚያደርጉ አስጠነቀቁ
በጋዛ ተኩስ አቁም እንዲደረግ በተመድ የጸጥታው ምክርቤት የቀረበው የውሳኔ ሀሳብ በአሜሪካ ተቃውሞ ሞክንያት ሳይጸድቅ ቀርቷል
እስራኤል በበኩሏ በመርከቦች ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት "የኢራን የሽብር ድርጊት" አለምአቀፍ የማሪታይም ደህንነትን የሚጎዳ ነው ብላለች
የሀውቲ ታጣቂዎች ወደ እስራኤል የሚያቀኑ ሁሉንም መርከቦች ኢላማ እንደሚያደርጉ አስጠነቀቁ።
የየመን ሀውቲ ታጣቂዎች ወደ እስራኤል የሚያቀኑ ሁሉንም መርከቦች እናጠቃለን ሲሉ ከእስራኤል ወደቦች ጋር ስምምነት ያደረጉ አለምአቀፍ የመርከብ ኩባንያዎችን አስጠንቅቀዋል።
በኢራን የሚደገፉት የሀውቲ ታጣቂዎች በቀጣናው ግጭት ይነሳል የሚለውን ስጋት ከፍ አድርገውታል።
ታጣቂዎቹ በቀይ ባህር እና አብዛኛው የአለም ነዳጅ በሚንቀሳቀስበት በባብኤል ማንደብ መስመር ላይ ከእስራኤል ጋር ግንኙነት አላቸው ባሏቸው በርካታ መርከቦች ላይ ጥቃት ጥቃት አድርሰዋል።
የሆውቲ ባለስልጣናት ጥቃቱን የሚፈጽሙት ለፍልስጤማውያን ድጋፋቸውን ለማሳየት እንደሆነ ተናግረዋል።
እስራኤል በበኩሏ በመርከቦች ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት "የኢራን የሽብር ድርጊት" አለምአቀፍ የማሪታይም ደህንነትን የሚጎዳ ነው ብላለች።
የሆውቲ ጦር ቃል አቀባይ ወደ እስራኤል ወደቦች የሚያቀኑ ሁሉም መርከቦች ከቀይ ባህር እና ከአረቢያን ባህር መታገዳቸውን ገልጿል።
ቃል አቀባዩ ጋዛ ምግብ እና መድሃኒት የማታገኝ ከሆነ በቀይ ባህር ወደ እስራኤል የሚያቀኑ ሁሉም መርከቦች የማንም ቢሆኑ የሀውቲ ጦር ኢላማ ናቸው ብሏል።
እገዳው ወዲያውኑ ተግባራዊ እንደሚሆን ቃል አቀባዩ ገልጿል።
ታጣቂዎቹ በቅርቡ ከእስራኤል ጋር ግንኙነት አላት ያሏትን አንድ መርከብ በቁጥጥራቸው ስር ሲያውሉ የሚያሳይ ቪዲዮ መልቀቃቸው ይታወሳል።
በጋዛ ተኩስ አቁም እንዲደረግ በተመድ የጸጥታው ምክርቤት የቀረበው የውሳኔ ሀሳብ በአሜሪካ ተቃውሞ ሞክንያት ሳይጸድቅ ቀርቷል።