ቻይና በራሷ የሰራችው አውሮፕላን መንገደኞችን አሳፍሮ የመጀመሪያው በረራ አድረገ
አውሮፕላኑ 130 መንገደኞችን አሳፍሮ ከሻንጋይ ወደ ቤጂንግ የ3 ሰዓት በረ አድርጓል
የC919 አውሮፕላን አምራች ኮማክ ኩባያ የ1 ሺሀ 200 የአውሮፕላን ምርት ትእዛዝ መቀበሉን አስታውቋል
ቻይና በራሷ አቅም የሰራቸው የመንገደኞች አውሮፕላን መንገደኞችን አሳፍሮ የመጀመሪያ የተሳካ በረራ ማድረጉ ተገለፀ።
አውሮፕላኑ 130 መንገደኞችን በማሳፈር ከሻንጋይ ወደ ቤጂንግ ከተማ የተሳካ በረራ ማድረጉ ነው የተገለፀው።
የC919 አውሮፕላን ዛሬ ጠዋት ላይ ከሻንጋይ ወደ ቤጂንግ ያደረገው የመጀመሪያው የንግድ በረራ 3 ሰዓት እንደፈጀበትም ተነግሯል።
አውሮፕላኑ ከቤጂንግ ወደ ሻጋይም መነገደኞችን በማሳፈር ተመሳሳይ በረራ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።
መቀመጫውን ሻንጋይ ያደረገው የቻይና የንግድ አውሮፕላን ኮርፖሬሽን (ኮማክ) የተመረተው C919 አውሮፕላን የቦይንግን እና ኤር ባስን የበላይነት ይሰብራል በሚል ተስፋ ተጥሎበታል።
ሆኖም ግን ባለ164 መቀመጫው C919 የመንገደኞች አውሮፕላን ሞተሩን ጨምሮ ሌሎቸ አካላቱን ከሌሎች ሀገራት የሚያመጣ በመሆኑ ጋር ተያይዞ አሁንም ምእራባውያን ተቋማት ላይ ጥገኛ አድርጎታል ተብሏል።
አሁን ላይ አውሮፕለኑ እንዲመረትላቸው በርካታ ተቋማት ጥያቄ እያቀረቡ ሲሆን፤ በቻይና መንግስት የሚተዳደረው ቻይና ኢስተርን አየር መንገድ 5 አውሮፕለኖች እንደሚረቱለት ጥያቄ አቅርቧል።
- ቻይና የሰራቻቸውን የመንገደኛ አውሮፕላኖች በያዝነው የፈረንጆቹ ዓመት ለገበያ ማቅረብ ልትጀምር ነው
- ለቻይናውያን ተማሪዎች የተዘጋጁ የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መጽሃፍት ተመረቁ
በቀጣይ 5 ዓመታት ውስጥ በየዓመቱ 150 አውሮፕላኖችን የማምረት እቅድ ያለው የቻይና የንግድ አውሮፕላን ኮርፖሬሽን (ኮማክ) እስካሁን 1 ሺህ 200 የC919 አውሮፕላን ምርት ትእዛዝ መቀበሉን አስታውቋል።
የአውሮፕላን ምርት እንዲስትሪው በቢሊየን ዶላሮች የሚንቀሳቀስ ሲሆን፤ የአሜሪካው ቦይንግ እና አፈረንሳዩ ኤር ባስ ይህንን ኢንደስትሪ በበላይነት እንደሚመሩት ይታወቃል።
`C919` የሚል ስያሜ የተሰጠው አዲሱ የቻይና አውሮፕላን ወደ ገበያ ሲቀላቀል ለእነዚህ ግዙፍ የአውሮፓላን አምራቾች አዲስ ተፎካካሪ ይሆናል ተብሏል።
`C919` አውሮፕላን ከ158 እስከ 168 መቀመጫውች ያሉት ሲሆን፤ እስክ 12 ሺህ 100 ሜትር ከፍተታ ድረስ መብረር የሚችል መሆኑም ነው የተገለፀው።
በሰዓት እስከ 900 ኪሎ ሜትር የሚበረው አውሮፕላኑ፤ በአንድ ጊዜ ከ4 ሺህ 75 እስከ 5 ሺህ 555 ኪሎ ሜትር መብረር የሚችል መሆኑም ተነግሯል።
ቻይና ኢስተርን አየር መንገድ አምስት `C919` የመንገደኞች አውሮፕላን ከቻይና የንግድ አውሮፕላን ኮርፖሬሽን ለመግዛት መፈራረሙ ታውቋል።