ቻይና በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ዜጎቿን ሰንደቅአላማዋን ዝቅ በማድረግ አስባቸዋለች
ቻይና በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ዜጎቿን ሰንደቅአላማዋን ዝቅ በማድረግ አስባቸዋለች
ቻይና በኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ በሽታ የሞቱ ዜጎቿን በዛሬው እለት ያሰበች ሲሆን በስነስርአቱ ላይ የቻይና ፕሬዘዳንት ዢ ጅንፒንግ ከሌሎች መሪዎች ጋር ሆነው ተገኝተዋል፡፡
ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ላይ የሶስት ደቂቃ የህሊና ጸሎት በማድረግ በኮሮና ቫይረስ/ኮቪድ19 የሞቱት ታስበዋል፡፡ በቻይና 3326 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡
ቻይናውያን በሀገሪቱ ሰንደቅአላማ ፊት ሆነውና ነጭ አበባ ደረታቸው ላይ አድርገው በሞት የተለዩትን ሰዎች በሶስት ደቂቃ ጥሞና አስበዋል፡፡
የህሊና ጸሎቱ በመላ ሀገሪቱ የተከናወነ ሲሆን የትራፊክ መብራት ቀይ በርቶ መኮኖች፣ባቡሮችና መርከቦች ቆመው ነበር፡፡
የበሽታ ወረርሽኝ በቻይና ሀገራዊ ሀዘን ሲያስከትል ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡
ቻይና ሰንደቅአላማ ዝቅ የማድረግ ህግ ተግባራዊ መሆን ከጀመረ በኋላ ሶስት ብሄራዊ ሀዘን ቀን ያወጀችው በፈረንጆቹ በ2008 ወንቹዋን በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ፣ በፈረንጆቹ 2012 ተከሰተውን የዩሹ መሬት መንቀጥቀጥንና በፈረንጆቹ በ2010 የከሰተውን ናዳ ተጎችን ለማሰብ መሆኑን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
በቻይና የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመቆጣጠር ጥረት ሲያደርጉ የነበሩ 40 ሰዎች ሞተዋል፤ እነዚህንና ሌሎች ዜጎቿን ለማስብ ቻይና በመላ ሀገሪቱና የቻይና ኢምባሲዎች በሚገኙባቸው ሀገራት ሰንደቅአላመዋ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ ተደርጓል፡፡
በቻይና ሁቤ ግዛት የተቀሰቀሰውናከ205 ሀገራት በላይ ያዳረሰው ኮሮና ቫይረስ 3326 ቻይናውያና ህይወታቸውን እንዲያጡ ምክንያት ሆኗል፡፡ በቻይና በአጠቃላይ 81,639 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘው ነበር፡፡