የቻይና ሳይበር ስፔስ አድሚንስትሬሽን ማብራሪያ ባይሰጥም መተግበሪያዎቹ አንድ ወይም ሁለት የሳይበር ህጎችን ጥሰዋል ብሏል
ቻይና የሀገሪቱን አፕስቶር ለማጽዳት በጀመረችው ዘመቻ የአሜሪካውን ትሪፕአዲቫይዘር ጨምሮ 105 የሚሆኑ መተግሪያዎችን አስወግዳች፡፡ ቻይና ይህን ያደረገችው የወሲብ፣ የቁማርና ብጥብጥ ይዘት ያላቸው መረጃዎች እየተሰራጩበት ነው በሚል ምክንያት እንደሆነ ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
የቻይና ሳይበር ስፔስ አድሚንስትሬሽን ባወጣው መግለጫ ግልጽ ማብራሪያ ባይሰጡም መተግበሪያዎቹ አንድ ወይም ሁለት የሳይበር ህጎችን ጥሰዋል ብለዋል፡፡ ሮይተርስ የትሪፕአዲቫይዘርን የቤጂንግ ቢሮ ለማናገር የሞከረ ቢሆንም ምላሽ አለማግኘቱን ገልጿል፡፡
ባለስልጣኑ እንዳስታወቀው ዘመቻውን የጀመረው በፈረንጆቹ ህዳር 5 ሲሆን እርምጃው የተወሰደው ህዝቡ እየወጡ ያሉት ይዘቶች የሚያስቀይሙ ናቸው የሚል ቅሬታ በማቅረቡ ነው ብሏል፡፡ መግለጫው እንዳለው መተግበሪያዎችን እንሚቆጣጠርና የህግ ጥሰት በሚፈጽሙት ላይ አስቸኳይ እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል፡፡
ቻይና ጥብቅ የሳይበር ቁጥጥር የምትከተል ሲሆን ህግ በሚጥሱ ላይ እርምጃ መወሰዷ የተለመደ ነው፡፡