ሩሲያ እና ቻይና ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ያለመ የመከላከያ እና ወታደራዊ ውይይት አደረጉ
"ወሰን የለሽ" ያሉትን ግንኙነታቸውን እያጠናከሩ ያሉት ሞስኮ እና ቤጂንግ አሜሪካ በእስያ ተጽእኖዋን ለማስፋት እየሰራች ነው ሲሉ ተችተዋል
በዚህ አመት ባለፈው ግንቦት ወር ሁለቱ የአሜሪካ ተቀናቃኞች ፑቲን እና ሺ አዲስ የግንኙነት ምዕራፍ ለመክፈት ቃል ገብተዋል
ሩሲያ እና ቻይና ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ያለመ የመከላከያ እና ወታደራዊ ውይይት አደረጉ።
ሁለቱ የእስያ ኃያላን ሩሲያ እና ቻይና ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ያለመ የመከላከያ እና ውታደራዊ ንግግሮችን ማድረጋቸውን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር በዛሬው እለት አስታውቋል።
"ወሰን የለሽ" ያሉትን ግንኙነታቸውን እያጠናከሩ ያሉት ሞስኮ እና ቤጂንግ አሜሪካ በእስያ ተጽእኖዋን ለማስፋት እየሰራች ነው ሲሉ ተችተዋል።
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር፣ መከላከያ ሚኒስትሩን አንድሬ ቤሎሶቭን ጠቅሶ በቴሌግራም ገጹ ላይ ባወጣው መግለጫ" የሁለቱ ሀገራት ወታራዊ ክፍሎች አንድ አይነት አለምአቀፋዊ ግምገማ እና በአሁናዊ ሁኔታዎች ምን መደረግ አለበት በሚለው ጉዳይም ተመሳሳይ አረዳድ ያላቸው ናቸው" ብሏል።
ቤሎሶቭ ከቻይና ሰንትራል ሚሊታሪ ኮሚሽን ምክትል ሊቀመንበር ጋር ተገናኝተው በወሳኝ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ተናግረዋል። ከስብሰባው በኋላ የቻይና መከላከያ ሚኒስቴር ሁለቱ አካለት ወታደራዊ ግንኙነታቸውን እንደሚያጠናክሩ እና እንደሚያስፋፉ እና በከፍተኛ ባለስልጣናት ደረጃ ያለውን የመረጃ ልውውጥ ባለበት እንደሚያስቀጥሉ ተስፋ እንዳለው ገልጿል።
ቤሎሶቮ በቤጂንግ ጉብኝት ያደረጉት ቻይና አስፈላጊ ከሆነ በታይዋን ላይ የኃይል እርምጃ እንደምትወስድ በዛተችበት ወቅት ነው።
ቻይና በታይዋን ዙሪያ 125 የጦር አውሮፕላኖችን እና የጦር መርከብ በመጠቀም ግዙፍ የተባለ የጦርነት ልምምድም አድርጋለች።
ፕሬዝደንት ፑቲን በየካቲት 2022 በዩክሬን ልዩ ላሉት ወታደራዊ ዘመቻ ጦራቸውን ከማሰማራታቸው ከሶስት ሳምንታት ቀደም ብለው በቤጂንግ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ነበር ቻይና እና ሩሲያ "ወሰን የለሽ" ግንኙነት ለማድረግ መወሰናቸውን ይፋ ያደረጉት።
በዚህ አመት ባለፈው ግንቦት ወር ሁለቱ የአሜሪካ ተቀናቃኞች ፑቲን እና ሺ አዲስ የግንኙነት ምዕራፍ ለመክፈት ቃል ገብተዋል።
ፑቲን እና ሺ ስትራቴጂካዊ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር መስማማታቸውን የገለጹት ቤሎሶቭ "ዉጤታማ እና ከባድ ውሳኔዎች ይጠበቃሉ" ብለዋል።
አሜሪካ ቻይና ሩሲያ በዩክሬን ለምታደርገው ጦርነት ጥቅም ላይ የሚውሉ ጎብአቶችን እያቀረበች ነው የሚል ክስ እያቀረበች ነው። ቻይና የጦር መሳሪያ ለየትኛውም አካል አመሰጠቷን እና ከሩሲያ ጋር ያላት የንግድ ግንኙነት ሊቆም ወይም ሊቋረጥ እንደማይገባ ገልጻልች።