ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በቻይና ቆይታቸው ከሀገሪቱ ፕሬዝዳንትና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር የወወያያሉ
የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለይፋዊ የስራ ጉብኘት ቻይና ገብተዋል።
ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና ልኡካቸው ቻይና ቤጂንግ ሲደርሱም የቻይና ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሱን ዌዶንግ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በቤጂንግ ቆይታው ከቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ እና ከሀገሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ጋር በነገው እለት ተገናኝተው እንደሚወያዩም የኤርትራወ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል አስታውቀዋል።
የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ወደ ቤጂንግ ያቀኑት ያቀኑት ከቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ በቀረበላቸው ግብዣ እንደሆነ ይታወሳል።
የቻይና የቀድሞ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ባሳለፍነው ጥር ውወ በኤርትራ ይፋዊ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ የተላከ መልእክት ለፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈረወርቂ ማቀበላቸው ይታወሳል።
በመልእክቱም የቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ ፐሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በቻይና ጉብኝት እንዲያደርጉ ግብዣ ማቅረባቸው ይታወሳል።
የቻይናው ከፍተኛ ዲፕሎማት ዋንግ ዪ በኤርትራ በነበራቸው ቆይታ ቻይና ለኤርትራ ተጨማሪ የ100 ሚሊየን ዩዋን ድጋፍ ማድረጓን ገልጸዋል።
ሁለቱ ወገኖች በማዕድን ልማት፣ በምፅዋና አሰብ ወደቦች ልማት፣ በሰው ኃይል አቅም ግንባታ እና በመሰረተ ልማት ዘርፍ በጋራ ለመስራትም ከስምምነት መድረሳቸውም አይዘነጋም።