ኢኮኖሚ
በቻይና የተመዘገበው የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ከአንድ ትሪሊዮን ይዋን በላይ ደረሰ
በፈረንጆቹ 2020 በቻይና የተመዘገበው የውጭ ኢንቨስትመንት 999 ነጥብ 98 ቢሊዮን ይዋን ነበር
በቻይና የተመዘገበው የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ከባለፈው አመት ጀምሮ እድገት ማሳየቱን የሀገሪቱ የንግድ ሚኒስቴር ገለጸ
ከባለፈው ዓመት ጀምሮ በቻይና የተመዘገበው የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ከፍተኛ ዕድገት ማሳየቱን የሀገሪቱ የንግድ ሚኒስቴር ይፋ አደረገ፡፡
በፈረንጆቹ 2021 መጀመሪያ እስከ ኅዳር ወር ድረስ በቻይና የተመዘገበው የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ከቀደመው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ 15 ነጥብ 9 በመቶ ብላጫ አለው ተብሏል፡፡
ባለፉት 11 ወራት ውስጥ በሀገሪቱ የተመዘገበው የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት አንድ ነጥብ 04 ትሪሊዮን ይዋን ወይም 163 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር መሆኑን ሲጂቴኤን ዘግቧል፡፡
የቻይና ንግድ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ቀደም ሲል በአውሮፓውያኑ 2021 የሚመዘገበው የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ከአንድ ትሪሊዮን ይዋን እንደሚበልጥ ተናግረው ነበር፡፡
በፈረንጆቹ 2020 በቻይና የተመዘገበው የውጭ ኢንቨስትመንት 999 ነጥብ 98 ቢሊዮን ይዋን የነበረ ሲሆን በአውሮፓውያኑ 2001 ወደ ቻይና የገባው ቀጥታ ኢንቨስትመንት 338 ቢሊዮን ይዋን እንደነበርም ተጠቅሷል፡፡