የቻይና “J-20” ተዋጊ ጄቶችን ምን የተለየ ያደርጋቸዋል…?
ቻይና ጄ-20 (J-20) የተባለ ዘመናዊ ተዋጊ ጄቶቿን ለቁጥጥር ስራ ወደ ምስራቅና ደቡብ ቻይና ባህር ላይ ማሰማራቷን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
ቻይና ጄ-20 የተባሉ ዘመናዊ ተዋጊ ጄቶቿን ከፍተኛ ውዝግብ ወዳለበት ስፍራ ያሰማራችው የሀገሪቱን የማሪታይም ብሄራዊ ይቅም ለማስጠበቅ እና የአየር ክልሏን ደህንነት ለማስጠበቅ እንሆነ ገሎባል ታይምስ አግቧል
የጄ-20 የተዋጊ ጄቶች አማራች ኩባንያ ቃል አቀባይ ሬን ዩኩን፤ ስምሪቱ አዲስ የቻይና ሞተር ተገጠመላቸው ጄ-20 ጄቶች የልምምድ አንድ አካል መሆኑን አስታውቀዋል።
ቻይና ጄ-20 የተዋጊ ጄቶቿን ምስራቅና ደቡብ ቻይና ባህር ላይ ማሰማራቷን ይፋ ያደረገችው የዩናይትድ ስቴትስ የፓስፊክ አየር ሃይል አዛዥ ጄኔራል ኬኔት ዊልስባች የአሜሪካ F-35 እና የቻይና J-20 ተዋጊ ጄቶች በምስራቅ ቻይና ባህር ላይ እጅጉን ተቀራርበው እንደበረሩ ማሳወቃቸውን ተከትሎ ነው።
ቻይና ጄ-20 (J-20) ተዋጊ ጄቶቿን ማሰማራቷ ሁለት ነገሮችን ያመለክታል ያሉ ሲሆን፤ ይህም ቻይና በመከላከያ አቅሟ ያላትን መተማመን የደረሰበትን ደረጃ እና ከሀገሪቱ ጋር የድንበር ግጭት ውስጥ ለሚገቡት ደግሞ ማስጠንቀቂያ ነው ብለዋል።
የቻይና “J-20” ተዋጊ ጄቶችን ምን የተለየ ያደርጋቸዋል…?
“J-20” ተዋጊ ጄቶች የመጀመሪያዎቹ ስሪቶች በሩሲያ የተመረቱ ሞተሮችን ይጠቀሙ የነበረ ሲሆን፤ በኋላ ላይ ግን ቻይና በራሷ ባመረተችው መንትያ ሞተር እንደተካች ይነገራል።
በችንግዱ ኤርክራፍት ግሩፕ የሚመረተው “J-20” ተዋጊ ጄት የመጀመሪያ በረራውን በፈረንጆቹ 2011 ያካሄደ ሲሆን፤ በ2017 በስራ ላይ እንደዋለም ተነግሯል።
በሰዓት እስከ 2 ሺህ 100 ኪሎ ሜትር ድረስ መብረር ይችላል የተባለለት “J-20” ተዋጊ ጄት፤ 19 ሺህ 390 ኪሎ ግራም ክብደት አለው ተብሏል።
“J-20” ተዋጊ ጄት ቻይና የዓለማችን ቀዳሚ ስውር ተዋጊ ጄት ተብለው ለሚነገርላቸው የአሜሪካ ኤፍ-22 እና ኤፍ-35 ተዋጊ ጅቶች የሰጠችው ምለሽ መሆኑ ይነገራል።
በአሁኑ ወቅት 200 J-20 ተዋጊ ጄቶች የቻይና ህዝቦች ነጻነት ሰራዊት ተብሎ በሚጠራው የቻይና ጦር አየር ኃይል አገልግሎት እየሰጡ ነው።
የቻይና አየር ክልሏ ለሚጥሱ የማንኛውም ሀገር ተዋጊ ጄቶች ምለሽ የምትሰጠው በእነዚሁ “J-20” ተዋጊ ጄቶች መሆኑ ተገልጿል።