በ5 ደቂቃ ውስጥ ከ480 ኪሎ ሜትር በላይ የተጓዘው አዲሱ የአሜሪካ ሃይፐርሶኒክ ሚሳዔል
ሃይፐርሶኒክ ሚሳዔል በሰዓት ከ6 ሺክ ሊሎ ሜትር በላይ መጓዥ ይችላል
አሜሪካ ከሰሞኑ አዲስ ሚስጥራው የሃይፐርሶኒክ ሚሳዔል ሙከራ አድርጋለች
የአሜሪካ ጦር ባሳለፍነው የፈረንጆቹ ወር ሚስጥራዊ የሃይፐርሶኒክ ሚሳዔል ሙከራ ማድረጉ ተሰምቷል።
ጦሩ የሚሳዔል ሙከራውን ለሁለት ሳምንታት ሚስጥራዊ አድርጎ የቆየው ከሩሲያ ጋር ያለው ያለውን ውጥረት ላለማባባስ እንደሆነም ዴይሊ ሜይል ዘግቧል።
አሜሪካ የሃይፐርሶኒክ ሜሳዔል ሙከራውን ያካሄደችው በምእራብ የባህር ዳርቻ ላይ ሲሆን፤ ሙከራውም ከ B-52 ቦምብ ጣይ የጦር አውሮፕላን ላይ መካሄዱ ታውቋል።
በሙከራው ወቅትም ሚሳዔሉ በ65 ሺህ ጫማ ከፍታ ላይ ከ480 ኪሎ ሜትር በላይ የተጓዘ ሲሆን፤ በአጠቃላይ 5 ደቂቃ ያክል አየር ላይ መቆየቱም ነው የተገለፀው።
አዲሱን የአሜሪካ ሃይፐርሶኒክ ሜሳዔል ምን የተለየ ያደርገዋል?
“ሃይፐርሶኒክ” የሚለው ቃል ከድምፅ እስከ 15 እጥፍ የሚፈጥን ማንኛውም ነገር የሚገልጽ ሲሆን፤ በሰዓት 6 ሺህ ኪሎ ሜትር ወይም ከዚያ በላይ የሚበር፤ በሌላ አገላለጽ እጅግ በጣም ፈጣን የሚለውን ለመግለጽ ጥቅም ላይ ይውላል።
አሜሪካ ከሰሞኑ የሞከረችው ሚሳዔልም ከጦር ጀቶች ላይ የሚወነጨፍ ሲሆን፤ ከድምፅ እስከ 15 እጥፍ የሚፈጥን መሆኑ ተነግሯል።
በዚህም ሚሳዔሉ በ5 ደቂቃ ውስጥ ከ480 ኪሎ ሜትር በላይ በሰዓት ደግሞ ከ6 ሺህ 173 ኪሎ ሜትር በላይ መብረር የሚችል መሆኑ ታውቋል።
ሚሳዔሉ በውጊያ ላይ ኢላማን ጠብቆ ለመዋጋት ወደር የለውም የተባለ ሲሆን፤ ሚሰዔሉን መትቶ መጣል ከባድ መሆኑም ተነግሮለታል።