“አውሬው” የሚል መጠሪያ የተሰጠው የቻይና “TB-001” የውጊያ ድሮን
ባለ ሁለት ጭራው ስኮርፒዮን ድሮን ሚሳዔሎችን በመታጠቅ ጠላትን የማጥቃት አቅም አለው
በአንድ ጊዜ እስክ 8 ሺህ ኪ.ሜ ርቀት የሚጓዝ ሲሆን፤ ለ35 ሰዓታት አየር ላይ ይቆያል
“አውሬው” የሚል መጠሪያ የተሰጠው የቻይና “TB-001” የውጊያ ድሮን ቻይና አሉኝ ከምትላቸው የጦር መሳሪያዎች ውስጥ አንዱ ነው።
ስኮርፒዮን (ጊንጥ) የውጊያ ድሮኑ ከባድ ቦምብ ጣይ እና ሚሳዔል አስወንጫፊ ሞዴል ጦር መሳሪያ መሆኑን ኢዮሩኤዢያን ታይምስ አስንብቧል።
ባለ ሶስት ሞተሩ “TB-001” የውጊያ ድሮን ለመጀመሪያ ጊዜ የተዋወቀው በፈረንጆቹ 2017 ሲሆን፤ የቻይና ጦር ከ2021 ጀምሮ እንደታጠቀው ተነግሯል።
“TB-001” የውጊያ ድሮን ባለ መንትያ ጭራው ጊንጥ (ስኮርፒዮን) በሚል የሚታወቅ ሲሆን፤ መቀመጫውን ሲቹዋን ባደረገው ቴንጎን የቴክኖሎጂ ኩባንያ የተሰራ ነው።
ድሮኑ በአንድ ጊዜ በረራ ከ6 ሺህ እስክ 8 ሺህ ኪሎ ምትር ድረስ የመብረር ብቃት ያለው ሲሆን፤ ከፍተኛ የአየር ላይ ቆይታ ሰዓቱም እስክ 35 ሰዓታት ነው።
“አውሬው” የሚል መጠሪያ የተሰጠው የቻይና “TB-001” የውጊያ ድሮን ሚሳዔሎችን እና ቦምቦችን በመታጠቅ ጠላትን የማጥቃት አቅም አለው።
ድሮኑ ከሚታጠቃቸው ሚሳዔሎች ውስጥም 20 ኪሎ ግራም የሚመዝነው “AR-2” ከሰማይ ወደ ሚድር የሚተኮስ ሚሳዔል አንዱ ሲሆን፤ ሚሳዔሉ ቀለል ያሉ በመድር ላይ ያሉ የጠላት ተሸከርካሪዎችን እና የግል መገልገያዎችን ለማጥቃት የሚውል ነው።
80 ኪሎ ግራም የሚመዝነው “AR-4” ከሰማይ ወደ ሚድር የሚተኮስ ሚሳዔል ሌላኛው ድሮኑ የሚታጠቀው የጦር መሳሪያ ሲሆን፤ ከበድ ያ ወታደራዊ ኢላማዎችን ለማጥቃት የሚውል ነው።
“AR-4” ሚሳዔል በ20 ኪሎ ሜትር ክልል ውስጥ ያለን ኢላማ መምታት የሚችል ሲሆን፤ ከ7 ሺህ ሜትር ከፍታ ላይ መተኮስ የሚችል መሆኑም ተነግሯል።
“TB-001” የውጊያ ድሮን ቻይና በታይዋን ውስጥ ወታደራዊ ዘመቻ ካካሄደች በቀዳሚነት አገልግሎት ላይ ከሚውሉ የጦር መሳሪያዎች መካከል አንዱ ሊሆን እንደሚችል ታውቋል።