“ዛዲራ” በ5 ሰከንድ ውስጥ ድሮን በአየር ላየ የሚያጋየው የሩሲያ የጦር መሳሪያ
“ዛዲራ” የሩሲያ የአዲስ ትውልድ የሌዘር የአየር መከላከያ የጦር መሳሪያ ስርዓት ነው
ሩሲያ በዩክሬን ጦርነት ላይ ካሰለፈቻቸው መሰሪያዎች ውስጥ “ዛዲራ” አንዱ ነው
ሩሲያ ከዩክሬን ጋር እያካሄደች ባለው ጦርነት ላይ ካሳለፈቻቸው የጦር መሳሪያዎች ውስጥ “ዛዲራ” የተባለው ሚስጥራዊ የአዲሱ ትውልድ የጦር መሳሪያ አንዱ ነው።
ሞስኮ ከምትጠቀማቸው የጦር መሳሪያዎች ውስጥ አንዱ የሆነው ዛዲራ የሌዘር (የጨረር) ስርዓት የሚጠቀም መሆኑ ተነግሯል።
ሩሲያ መሳሪያውን ለመጀመሪያ ጊዜ ያሳየችው በጥቁር ባህር ላይ በሩሲያ ቁጥጥር ስር የሚገኘውን ስኔድ ደሴት ላይ ዩከሬን ባይታካር በተባሉ የቱርክ ድሮኖች ተጠቅማ የሰነዘረችውን ጥቃት በመከተችት ጊዜ ነው።
የሩሲያው ፕሬዝዳት ቭላድሚር ፑቲን ባሳለፍነው ግቦት ወር ላይ ባደረጉት ንግግር፤ የሩሲያ ጦር የረቀቁ ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎች መጠቀም ጀምሯል ማለታቸው ይታወሳል።
ሞስኮ ይፋ ያደረገችው አዲሱ መሳሪያ የአየር ክልልን የሚቆጣጠር ሲሆን፤ የጨረር ቴክኖሎጂ (ሌዘር) የሚጠቀም መሆኑ ተነግሯል።
“ዛዲራ” የተባለው የጦር መሳሪያ እስከ 5 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ያለውን ድሮን መለየት የሚችል ሲሆን፤ ከመሬት እስከ 1 ሺህ 500 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ጠንካራ የሳተላይት መከላከያ ስርዓት መገንብት ይችላል ተብሏል።
“ዛዲራ” ድሮኖችን በአየር ላይ እያሉ በ5 ሰከንዶች ውስጥ ያጋያል የተባለ ሲሆን፤ ሌሎች ወደ ሩሲያ የሚተኮሱ ሚሳዔሎች መከላከል ይችላል ተብሏል።