በዓለም ላይ ካሉ “በጣም አደገኛ” የጦር መርከቦች አንዱ የሆነው የቻይናው “ለሃሳ” መርከብ
መርከቡ የባህር ላይ ተልእኮዎችን የመፈጸም ሙከራውን በሙሉ አጠናቆ ለስምሪት ዝግጁ ሆኗል
መርከቡ ከምድር ወደ አየር ሚሳዔሎችን ጨምሮ የፀረ-መርከብና ፀረ-ሰርጓጅ ሚሳኤሎች ማስወንጨፍ ይችላል
የቻይና ሁለተኛው ዓይነት 055 ትልቅ አውዳሚ የጦር መርከብ ባህር ላይ ተልእኮዎችን የመፈጸም ሙከራውን በሙሉ ማጠናቀቁ ተገለፀ።
“ለሃሳ” የሚል መጠሪያ ያለው ሁለተኛው ዓይነት 055 የጦር መርከብ 10,000 ቶን ደረጃ ያለው ሲሆን፤ የአየር ላይ እና የባህር ላይ ጥቃት እንዲሁም ፀረ-ባሕር ውስጥ የማጥቃት አቅምን ባሟላ መልኩ የሙሉ ኮርስ የውጊያ ሥልጠና ግምገማ ማለፉ ተነግሯል።
የመጀመሪያው ለሃሳ የጦር መርከብ በፈረንጆቹ መጋት ወር 2021 ላይ ለአገልግሎት ዝግጁ የተደረገ ሲሆን፤ መርከቡ በሩቅ የባህር አካላት ላይ ትልእኮዎችን ለመፈጸም ዲዛይን የተደረገ ነው።
የዘርፉ ባለሙያዎች ለቻይና ሚዲያ ግሩፕ በሰጡት አስተያየት ላህሳ የጦር መርከብ የባሀር ላይ ተልእኮዎችን ለመፈጸም ሙሉ በሙሉ ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል።
የቻይና ባህር ኃይል አካ የመሆነው የባሀር መርከብ የልምምድ ማእከል ባዘጋጀው መርሃ ግብር ላይ ላህሳ የጦር መርከብ ከዓይነት ሶስት 056 የጦር ተዋጊ መርከቦች ጋር በመሆን በቢጫ ባህር ላይ የሶስት ቀናት ልምምድ ማድጉ ተነግሯል።
“ለሃሳ ዓይነት 055” የጦር መርከብ በዓለማችን ላይ ካሉ አደገኛ የጦር መርከቦች ውስጥ አንዱ እንደሚሆን ታምኗል።
መርከቡ 112 ወደላይ የሚሳዔል ማስወንጨፊያ ሴሎች ያሉት ሲሆን፤ በዚህም ከምድር ወደ ሰማይ ሚሳዔል ማስወንጨፍን ጨምሮ የምድር ላይ ጥቃት ሚሳዔሎችንን እንዲሁም የፀረ መርከብ እና የፀረ ሰርጓጄ መርከቦች ሚሳዔሎችንም ያስወነጭፋል።