ኮሮና የለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘባት ውሃን ከተማ ለሁሉም ነዋሪዎቿ የኮሮና ምርመራ ልታደርግ ነው
ቫይረሱ በቻይና የተለያዩ ከተሞች በፍጥነት እየተዛመተ እንደሆነም መረጃዎች ያመለክታሉ
በማእከላዊ ቻይና በትገኘው የውሃን ከተማ 11 ሚልዮን ህዝብ ይኖራል
የቻይናዋ ውሃን ከተማ በ'ሁሉም ነዋሪዎቿ' ላይ የኮቪድ-19 ምርመራ እንደምታደርግ የከተማዋ ባለስልጣናት አስታወቁ፡፡ የቻይናዋ ውሃን ከተማ የኮሮና ቫይረስ ለመጀመሪያ ጊዜ የተከሰተባዋት ከተማ መሆኗ ይታወቃል፡፡
11 ሚልዮን ህዝብ የሚኖርባትና የማእከላዊ ቻይና ከተማ የሆነችው ውሃን በመላ ህዝቧ ላይ ምርመራ የምታደርገው ከአንድ አመት በኋላ፤ በከተማዋ በሚገኙ ሰባት ስደተኛ ሰራተኞች ላይ የኮሮና ቫይረስ ኢንፌክሽን እንደተገኘ ሪፖርት መደረጉን ተከትሎ ነው፡፡
የውሃን ባለሥልጣኑ ሊ ታኦ “የሁሉም ነዋሪዎችን አጠቃላይ የኑክሊክ አሲድ ምርመራን በፍጥነት እየተጀመረ ነው” ሲሉ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ማስታወቃቸው የፈረንሳዩ የዜና ወኪል/ፍራንስ 24/ ዘግቧል፡፡
በወራት ውስጥ ትልቁ የኮሮኔቫ ቫይረስ ወረርሽኝን ለመዋጋት፤ ቻይና የሁሉም ከተሞች ነዋሪዎችን በቤታቸው እንዲሆኑ ገድባለች ፣ የሀገር ውስጥ የትራንስፖርት አቋርጣለች እንዲሁም በከፍተኛ የቁጥር መጠን ምርመራ ማካሄድ ጀመራለች፡፡
እስካሁን ድረስ በቻይና 61 ኢንፌክሽኖች የተገኙ ሲሆን ቫይረሱ በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ተለያዩ ከተሞች እየተዛመተ እንደሆነም መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ቤጂንግ እስካለሁን በሚልዮን በሚቆጠሩ ነዋሪዎች የኮቪድ-19 ምርመራ ካካሄዱ ከተሞች አንዷ ናት፡፡
40 አዳዲስ ኢንፌክሽኖች የተገኙባትና 1.3 ሚልዮን ህዝብ የሚኖርባት የምስራቅ ቻይናዋ ከተማ ያንግዙ ከተማም እንዲሁ ነዋሪዎችዋን በቤታቸው እንዲቆዩ በማድረግ ምርመራ በማካሄድ ላይ ናት፡፡
ዣንግጂያጂ እና ናንጂንግ ከተሞችም ተመሳሳይ እርምጃ እየወሰዱ ያሉ የቻይና ከተሞች ናቸው፡፡ቱሪስቶች ከቦታ ቦታ ሚያደርጉት እንቅስቃሴ ለጊዜው ገታ እንዲያደርጉም ነው ባለስልጣናት አሳስበዋል፡፡