የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከየካቲት ጀምሮ B737 ማክስ አውሮፕላንን ወደ በረራ እንደሚመልስ አስታወቀ
አውሮፕላኑ በኢትዮጵያ እና ኢንዶኔዢያ ከተከሰከሰ በኋላ 34 አየር መንገዶች ዳግም ወደ በረራ መልሰውታል
አውሮፕላኑ አሁን ላይ የነበሩበት የበረራ ደህንነነት ችግሮች መፈታቱን ዓለም አቀፍ ተቋማት ማረጋገጨ ሰጥተዋል
አየር መንገዱ እንዳሳወቀው ከመጭው የካቲት ወር ጀምሮ B737 የተሰኘውን ማክስ አውሮፕላን ወደ በረራ ይመለሳል፡፡
የአየር መንገዱ ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም እንዳሉት የበረራ ደህንነትን ማስጠበቅ የአየር መንገዱ ዋነኛ ትኩረት መሆኑን ገልጸው ዓለም አቀፍ የአቪዬሽን ደህንነት የጥራት ደረጃን ባሟላ መንገድ B737 ማክስ አውሮፕላን ወደ በረራ ይመለሳል ብለዋል፡፡
ኤር መንገዱ B737 ማክስ አውሮፕላንን ወደ በረራ የሚመልሰው በዚህ አውሮፕላን ላይ የነሱ የነበሩ ደህንነት ችግሮች መፈታታቸውን የአሜሪካ ፣ካናዳ እና እና አውሮፓ አቪዮሽን አስተዳድሮች መፈታታቸውን አረጋግጠዋል፡፡
አሁን ላይ B737 ማክስ አውሮፕላን 34 የዓለማችን አየር መንገዶች ወደ በረራ የመለሱት መሆኑን ተከትሎ የኢትዮጵያ አየር መንገድም ዳግም ወደ በረራ ሊመልሰው መሆኑን አስታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ አቪዬሽን ባለሙያዎች ለ20 ወራት በዚህ አውሮፕላን ላይ ባደረጉት ተከታታይ የበረራ ደህንነት ፍተሻ አውሮፕላኑ ለበረራ ዝግጁ መደረጉም ተገልጿል፡፡
ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነው ቦይንግ 737 ማክስ ኤይት አውሮፕላን መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ.ም ከቦሌ አውሮፕላን ጣቢያ ተነስቶ ወደ ኬንያ ናይሮቢ 157 ሰዎችን ጭኖ በማምራት ላይ እያለ ቢሾፍቱ አካባቢ ተከስክሶ ሁሉም መንገደኞች ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል፡፡