የአሜሪካ አፈጉባኤ በታይዋን ጉብኝት ማድረጋቸውን ተከትሎ ታይዋን እና ቻይና ውጥረት ውስጥ ገብተዋል
ታይዋን በትናንትናው እለት እንደገለጸችው ቻይና ድንበሯን ጥሳ ጥቃት የምትከፍት ከሆነ ራሷን ለመከላከል ወታደራዊ ልምምድ እንደምታካሂድና መልሶ ማጥቃት እንደምትሰነዝር ገልጻለች።
ታይዋን ይህን ያለችው ቻይና በደሴቷ ዙሪያ የምታደርገው ወታደራዊ እንቅስቃሴ በመጨመሯ ምክንያት ነው። ታይዋንን የግዛቷ አካል አድርጋ የምትቆጥረው ቻይና የአሜሪ አፈጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ ላደረጉት ጉብኝት አጸፋ በሚል ታይዋንን በመክበብ ወታደራዊ ልምምድ ማድረጓን ቀጥላለች።
የታይዋን መከላከያ ሚኒስትር ቻይና በታይዋን ዙሪያ የምታደርገው ወታደራዊ እንቅስቃሴ መጠናከሩን ገልጸዋል። ሚኒስትሩ የቻይና እንቅስቃሴ በቀጣናው አለመረጋጋት ይፈጥራልም ብለዋል።
የታይዋን ምክትል ኢታማጆር ሹም ለኦፕሬሽን እና እቅድ ሊን ዊንሀንግ የታይዋን ብሄራዊ ጦር ራስን የመከላከል እና የመልሶ ማጥቃት እንቅስቃሴ እንደሚያካሂድ ገልጸዋል።
በዚህ ወር ታይዋን ወታደራዊ ወጭዋ እንዲጨምር አድርጋለች።
ቻይና ታይዋንን የግዛቷ አካል አድርጋ የምታይ ሲሆን ከታይዋን ጋር ግንኙነት የሚያደርግ ማንኛውን ሀገር ሉአላዊነቷን እንደጣሰ አድርጋ ትቆጥራለች።
ቻይና ከአሜሪካ ጋር ያላትን ወታደራዊ ትበብር ማቋረጧም ይታወሳል።