ፖለቲካ
ኢማኑኤል ማክሮን በተቃውሞ የታመሰችውን ፓሪስን ለቀው ወደ ቻይና ሊያቀኑ ነው
የፈረንሳይ ተቃውሞ የእንግሊዝ ንጉስ ቻርለስ ጉብኝታቸውን እንዲሰርዙ አስገድዷል
ፈረንሳይ በቀውሷ መሀል ዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ መርሃ-ግብሯን ለማስቀጠል እየሞከረች ነው ተብሏል
የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን "ላልተለመደ ጉብኝት" በሚቀጥለው ሳምንት ወደ ቻይና ያቀናሉ ተብሏል።
ጉብኝቱ ሀገራቸው በጡረታ ማሻሻያ ተቃውሞ እየታመሰች ባለችበት ጊዜ የመጣ ነው።
- የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን በጉብኝት ላይ እያሉ በጥፊ ተመቱ
- ከማሊና ቡርኪና ፋሶ የተባረረችው ፈረንሳይ ሌላ አፍሪካዊ ሀገር ፍለጋ ላይ መሆኗን ገለጸች
በዚህ ወር መጀመሪያ በአወዛጋቢ የጡረታ ህግ በፈረንሳይ ከተሞች ግጭት እና ብጥብጥ ተቀስቅሷል።
ብጥብጡ የእንግሊዝ ንጉስ ቻርለስ ጉብኝታቸው እንዲሰርዙ አስገድዷል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።
የፈረንሳይ መንግስት ዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ መርሃ-ግብሩን ለማስቀጠል እየሞከረ ነው ተብሏል።
ማክሮን የአውሮፓ መሪ ለመሆን የሚያደርጉት ጥረት የዓለም ዲፕሎማሲ መድረኮች ያስፈልጋቸዋል ተብሏል።
ዲፕሎማቶች ቻይና በጉብኝቱ የምዕራቡ ዓለም ቡድንን ለመከፋፈልና ፈረንሳይን ከአሜሪካ ለማራቅ ትሞክራለች ብለዋል።
ማክሮን በበኩላቸው በቅርቡ ከሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ለመከሩት ዢ ጂንፒንግ፤ ቻይና ለሩሲያ የጦር መሳሪያ እንዳትሰጥ ግልጽ ማስጠንቀቂያ መስጠት ይፈልጋሉ ተብሏል።