ከታይዋን ጋር ይፋዊ ግንኙነት የመሰረቱ ሀገራት ቁጥር መመናመኑ ተገለጸ
የቻይና ተጽዕኖ እያየለ መምጣት ከታይዋን ጋር ግንኙነት የጀመሩ ሀገራት ቁጥር እንዲቀንስ ማድረጉ ተገልጿል
ከታይዋን ጋር ይፋዊ ግንኙነት የመሰረቱ ሀገራት ቁጥር መመናመኑ ተገለጸ
ከታይዋን ጋር ይፋዊ ግንኙነት የመሰረቱ ሀገራት ቁጥር መመናመኑ ተገለጸ፡፡
ቻይና የግዛቴ አንድ አካል ናት የምትላት ታይዋን ራሷን እንደ ሉዓላዊ ሀገር በመቁጠር ከተለያዩ ሀገራት ጋር ይፋዊ የዲፕሎማሲ ግንኙነትን በማድረግ ላይ ትገኛለች፡፡
ታይዋን በተለይም ከአሜሪካ እና ሌሎች ምዕራባዊያን ሀገራት ግልጽ ድጋፍ በማግኘት ላይ ስትሆን እስካሁን ዋሸንግተንን ጨምሮ ሌሎችም እውቅና አልሰጧትም፡፡
ይሁንና ከፈረንጆቹ 2016 ጀምሮ ግን ታይዋን ከ22 የተለያዩ ሀገራት ጋር ይፋዊ የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን መመስረቷን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ከታይዋን ጋር ይፋዊ ግንኙነት የጀመሩ ሀገራት ከቻይና ማስጠንቀቂያ የደረሳቸው ሲሆን አንዳንዶቹ ግንኙነታቸውን በማቋረጥ ላይ ናቸው፡፡
ለታይዋን የሀገርነት እውቅና ከሰጡ ሀገራት መካከል አንዷ የነበረችው የላቲን አሜሪካዋ ሆንዱራስ አሁን ፊቷን ወደ ቻይና ማዞሯን በይፋ አስታውቃለች፡፡
23 ሚሊዮን ህዝብ ብዛት ያላት ታይዋን ከአፍሪካ ከእስዋቲኒ ጋር ይፋዊ የዲፕሎማሲ ግንኙነትን ስትመሰርት ከአውሮፓ ደግሞ ቫቲካን ጋርም ተመሳሳይ ግንኙነት መስርታለች፡፡
በላቲን አሜሪካ ደግሞ ጓቲማላ፣ ሀይቲ ፣ፓራጓይ እና ሌሎች እንደ ታይዋን ሉዓላዊ ሀገር የመሆን ጥያቄ ካላቸው ትንንሽ ደሴቶች እና ሀገራት ጋር ግንኙነት እንዳላት ተገልጿል፡፡
ለሶስተኛ ጊዜ የቻይና ፕሬዝዳንት ሆነው የተመረጡት ዢ ፒንግ ታይዋን በሰላማዊ መንገድ ከቤጂንግ ጋር ውህደት እንድትፈጽም መጠየቃቸው ይታወሳል፡፡
ታይዋን በበኩሏ ጉዳዩ የ23 ሚሊዮን ህዝብ ፍላጎት በመሆኑ በሀይል የሚደረጉ ድርጊቶችን እንደማትቀበል አስታውቃለች፡፡
አሜሪካ በበኩሏ ቻይና ታይዋንን በሀይል የመጠቅለል እቅድ ይዛ እየተንቀሳቀሰች ነው በሚል ለታይዋን የጦር መሳሪያ እና ሌሎች ድጋፎችን በማድረግ ላይ ትገኛለች፡፡