ቻይና ሳተላይቶችን የሚያወድምን ጨምሮ እስክ ኒውክሌር ተሸካሚ ሚሳዔሎችን እየሞከረች ነው
ቻይና የሚተኮስባትን ሚሳዔል አየርላይ እያለ የሚያከሸፍ አዲስ ሚሳዔል የማስወንጨፍ ሙከራ ማድረጓ ተገለፀ።
የቻይና መከላከያ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ከምድር ወደ ሰማይ የሚወነጨፍው አዲሱ የሚሳዔል ስርዓት ሙከራው የተሳካ ነበር።
ሚሳዔሉ የታለመለትን አላ ማ ያሳካ ነው ያለው ሚኒስቴሩ፤ ቻይና እየሰራች ያለው ስራ ሌላ ሀገርን ለመጉዳት ሳይሆን ራስን መከላከልን ማእከል ያደረገ ነው ብሏል።
የሚሳዔል ሙከራው በትናትናው እለት ምሽት የተካሄደ ሲሆን፤ አዲሱ ሚሳዔል ወደ ቻይና የሚተኮስ ማንኛውም ሚሳዔል ኢላማውን ከመምታቱ በፊት አየር ላይ እያለ ጠለፋ በመፈጸም የሚያከሽፍ ነው።
ቻይና ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በሁሉም አይነት ሚሳዔሎች ላይ መርምሮችን እና ሙከራዎችን እያደረገእ እንደሆነ ተነግሯል።
ሀገሪቱ እየሰራችባቸው የሚሳዔል አይነቶች ውስጥም ሳተላይቶችን የሚያወድመውን ጨምሮ እስከ የኒውክሌር አረር ተሸካ ሚሳዔሎች ይገኙበታል ተብሏል።
ቻይና፣ ከአጋሯ ሩሲያ ጋር በመሆን አሜሪካ THAAD የአየር መከላከያ ሚሳኤልን በደቡብ ኮሪያ መትከሏን ተቃውሟቸውን ደጋግማ ስትገልጽ ቆይታለች።