10 ሜጋቶን ጦር የኒውክሌር አረር በ80 ኪ.ሜ ከፍታ ላይ ቢፈነዳ ሳተላይቶችን ሊያጠፋ ይችላል
ቻይና በጠፈር ላይ የሚገኙ ጠላት ሳተላይችን የማውደም አቅም ያለው አዲስ የኒውክሌር የጦር መሳሪያ መስራቷ ተነግሯል።
ቻይና የኒውክሌር ጦር መሳሪያን በመጠቀም ከምድር በመተኮሰ በጠፈር ላይ ያሉ ሳተላይቶችን ለማጥፋት የሚያስችል ልምምድ መጀመሯም ኤዢያን ታይምስ ዘግቧል።
አዲስ የፀረ ሳተላይት የኒውክሌር መሳሪያ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን ለመደገፍ የሚያገለግሉ በርካታ የጠላት የሳተላይቶችን ሊያጠፋ የሚችል መሆኑም ታውቋል።
በቻይና ጦር ስር በሚተዳደረው ኖርዝ ዌስት ኒውክሌር ኢኒስቲትዩ እየተሰራ ያለው መሳሪያው፤ የተለያዩ ከፍታዎች ላይ የሚገኙ ሳተለይቶችን የማጥፋት አሊያም የማውደም አቅሙ ባለው የኒውክሌር የጦር መሳሪያ ላይ ሙከራ እያደረገ ነው።
የኢኒስቲትዩቱ የተመራማሪዎች ቡድን ባደረጉት ሙከራም 10 ሜጋቶን ጦር የኒውክሌር አረር በ80 ኪ.ሜ ከፍታ ላይ ቢያፈነዳ ሳተላይቶችን የማጥፋ አቅም እንዳለው ታውቋል።
በፍንዳታ ወቅትራዲዮ አክቲቭ ቅንጣቶች የሚፈጠር ዳመና ሳተላይቶች ስራውን እንዳይከውኑ እና አንዲወድሙ የማድረግ አቅም ያለው መሆኑ ተመራማሪዎቹ ባወጡተ ጽሁፍ አስታውቀዋል።
ቻይና የተለያዩ አደዲስ የጦር መሳሪያዎችን እየሰራች ሲሆን፤ በቅርቡም አዲሰ የፀረ ድሮን ቴክኖሎጂ ይፋ ማድረጓ አይዘነጋም።
አዲሱ የፀረ ድሮን ስርዓት በጣም በአነስተኛ እና ጥቃቅን ሚሳኤሎች፣ የረቀቁ ሴንሰሮችን እና ራዳር በማካተት የተሰራ ነው።
በቻይና ኤሮስፔስ ሳይንስና ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የተሰራው አዲሱ ቴክኖሎጂ በአንድ ሰከንድ ውስጥ ከ500 ሜትር እስከ 18 ኪሎ ሜትር ርቀት ውስጥ የሚገኙ 20 የጠላት ኢላማዎችን መለየት እና ማጥቃት የሚችል ነው።