የቻይና “J-20” ተዋጊ ጄቶችን ምን የተለየ ያደርጋቸዋል…?
የ2022 የቻይና የአየር ትርኢት በደቡባዊ የሀገሪቱ ከተማ ዡሃይ መካሄድ ላይ ሲሆን፤ “J-20” ስውር ተዋጊ ጄት ለእይታ ቀርቧል።
የቻይና ሕዝብ ነፃ አውጪ ጦር ተብሎ የሚጠራው የቻይና ጦር የታጠቀው “J-20” ስውር ተዋጊ ጄቶች ዙሃይ ሰማይ ላይ መታየታቸው ለቻይና ኤር ሾው የበለጠ ድምቀትን ጨምሯል።
ለቻይና ኤር ሾው ላይ የቻይና አየር ሃይል ተዋጊዎች እና "የአየር ኤሮባቲክስ" ቡድን በዙሃይ ታላቅ የአየር ትርኢት ቢያቀርቡም አራት ጄ-20 ስውር ተዋጊዎች የተመልካችን አይን ስበዋ ነው የተባለው።
የቻይና “J-20” ተዋጊ ጄቶችን ምን የተለየ ያደርጋቸዋል…?
“J-20” ተዋጊ ጄቶች የመጀመሪያዎቹ ስሪቶች በሩሲያ የተመረቱ ሞተሮችን ይጠቀሙ የነበረ ሲሆን፤ በኋላ ላይ ግን ቻይና በራሷ ባመረተችው መንትያ ሞተር እንደተካች ይነገራል።
በችንግዱ ኤርክራፍት ግሩፕ የሚመረተው “J-20” ተዋጊ ጄት የመጀመሪያ በረራውን በፈረንጆቹ 2011 ያካሄደ ሲሆን፤ በ2017 በስራ ላይ እንደዋለም ተነግሯል።
በሰዓት እስከ 2 ሺህ 100 ኪሎ ሜትር ድረስ መብረር ይችላል የተባለለት “J-20” ተዋጊ ጄት፤ 19 ሺህ 390 ኪሎ ግራም ክብደት አለው ተብሏል።
“J-20” ተዋጊ ጄት ቻይና የዓለማችን ቀዳሚ ስውር ተዋጊ ጄት ተብለው ለሚነገርላቸው የአሜሪካ ኤፍ-22 እና ኤፍ-35 ተዋጊ ጅቶች የሰጠችው ምለሽ መሆኑ ይነገራል።
በአሁኑ ወቅት 200 J-20 ተዋጊ ጄቶች የቻይና ህዝቦች ነጻነት ሰራዊት ተብሎ በሚጠራው የቻይና ጦር አየር ኃይል አገልግሎት እየሰጡ ነው።
የቻይና አየር ክልሏ ለሚጥሱ የማንኛውም ሀገር ተዋጊ ጄቶች ምለሽ የምትሰጠው በእነዚሁ “J-20” ተዋጊ ጄቶች መሆኑ ተገልጿል።