ቻይና ሾፌሮች በስራ ላይ እያሉ እንዳይተኙ የሚያደርግ ቴክኖሎጂ ሰራች
ቴክኖሎጂው እያሽከረከሩ ያሉ ሾፌሮች ሲተኙ ደማቅ ብርሀን በማብራት የሚቀሰቅስ እንደሆነ ተገልጿል
የቴክኖሎጂውን ፈጠራ ተከትሎ በቻይና ዋነኛ መነጋገሪያ ሆኗል
ቻይና ሾፌሮች በስራ ላይ እያሉ እንዳይተኙ የሚያደርግ ቴክኖሎጂ ሰራች።
የሩቅ ምስራቋ ቻይና በተለይም በፈጠን መንገዶች ላይ የሚደርሱ የትራፊክ አደጋዎችን ለመቀነስ መላ መዘየዷ ተገልጿል።
በሀገሪቱ በተለይም በሌሊት ወቅት አሽከርካሪዎች በእንቅልፍ መውደቅ ለትራፊክ አደጋዎች ዋነኛው ምክንያት ነውም ተብሏል።
ይህን አደጋ ለመቀነስም አሽከርካሪዎች እንቅልፍ ሲጥላቸው አልያም የእንቅልፍ ስሜት ሲሰማቸው ደማቅ እና ንዝረት ያለው መብራት በማብራት እንዲነቁ የሚያደርግ ቴክኖሎጂ መፍጠሯን አስታውቃለች።
እንደ ቴክ ቻይና ዘገባ ከሆነ በሀገሪቱ ፈጣን መንገዶች ላይ ተሞክሮ ውጤታማ ሆኗል የተባለ ሲሆን አገልግሎቱ ለሁሉም አሽከርካሪዎች ክፍት መደረጉ ተገልጿል።
በእንቅልፍ የወደቀ ወይም እንቅልፍ ስሜት የተሰማው አሽከርካሪ በቴክኖሎጂው መሰረት መብራቱ ሲበራ እና ሲቀሰቅሰው የሚያሳየው ቴክኖሎጂ ተንቀሳቃሽ ምስል በማህበራዊ ትስስር ገጾች የተለቀቀው ቪዲዮ በትንሽ ጊዜ ውስጥ ከ56 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ተመልክተውታል ተብሏል።
ምስሉን የተመለከቱ ሰዎችም በቴክኖሎጂው ዙሪያ አስተያየታቸውን ያጋሩ ሲሆን ፈጠራው ጥሩ መሆኑን፣ ፈጠራው በአሽከርካሪው ላይ መደናገጥ የሚፈጥር ነው፣ ብርሀኑ ደማቅ እና ከባድ በመሆኑ ሌሎች አሽከርካሪዎች እንዳያዩ ያደርጋል እና መሰል አስተያየቶች እየተሰነዘሩም ይገኛሉ።