ቤጂንግ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫዋን ያገኘችትን 50ኛ ዓመት እያከበረች ነው
ቻይና ከዛሬ 50 ዓመታት በፊት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ጥበቃ ምክር ቤት ቋሚ አባልነን በዲጋሚ ስታገኝ ኢትዮጵያ የድጋፍ ድምጽ በመስጠቷ ምስጋና አቀረበች።
በአዲስ አበባ የሚገኘው የቻይና ኤምባሲ ባወጣዉ መግለጫ፤ ቤጂንግ የፀጥታው ጥበቃ ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫዋን ያገኘችትን 50ኛ ዓመት አስመልክቶ ኢትዮጵያን አመስግኗል።
ቻይና በተመድ የፀጥታው ጥበቃ ምክር ቤት ሕጋዊ መቀመጫ ይኑራት ወይስ አይኑራት የሚል ውሳኔ ሲሰጥ ኢትዮጵያ ድጋፍ በመስጠቷ ነው ቤጅንግ ያመሰገነችው።
ቤጅንግ አባል ስትሆን ድጋፍ ከሰጡ 76 ሀገራት አንዷ ኢትዮጵያ መሆኗን የጠቀሰው ኤምባሲው ኢትዮጵያ፤ ለቻይና ያደረገችው መቸም ቢሆን እንደማይረሳ ገልጿል።
ቻይና በማደግ ላይ ያለች ግዙፍ ሀገር በመሆኗ በመንግስታቱ ድርጅት የሚኖራት ውግንና ኢትዮጵያን ጨምሮ በማደግ ላይ ሀገራት መሆኑን ገልጻለች።
የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂን ፒንግ ቤጂንግ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫዋን ያገኘችትን 50ኛ ዓመት በማስመልከት በሰጡት መግለጫ፤ “በወቅቱ ከቻይና ጎን ለቆሙ ሀገራት በሙሉ በሀገሪቱ ህዝብ እና መንግስት ስም ላመሰግን እወዳለሁ” ብለዋል።
ሀገራቱ በወቅቱ ከፍትህ ጎን ስለቆሙ ተገቢውን ክብር እና እውቅና ሊያገኙ ይገባል ሲሉም ፕሬዝዳንት ሺ ጂን ፒንግ ተናግረዋል።