ቻይና የምድራችን ግዙፍ የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ መገንባት ጀመረች
በ34 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ቲቤት ግዛት ይገነባል የተባለው ይህ የሀይል ማመንጫ በዓመት 300 ቢሊዮን ኪሎዋት ሀይል ይመነጫል

የሀይል ማመንጫው ወደ ሕንድ እና ባንግላዲሽ ይፈስ በሚፈሰው ያርሉንግ ዛንግቦ ወንዝ ላይ ይገነባል ተብሏል
ቻይና የምድራችን ግዙፍ የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ መገንባት ጀመረች።
የዓለማችን ሁለተኛዋ ልዕለ ሀያል ሀገር የሆነችው ቻይና የምድራችን ግዙፍ የሀይል ማመንጫ ጣቢያን መገንባት ጀምራለች።
ፕሮጀክቱ በምስራቅ ቻይና በምትገኘው ቲቤት ግዛት ላይ ይገነባል የተባለ ሲሆን ግንባታው ሲጠናቀቅ በዓመት 300 ቢሊዮን ኪሎ ዋት ሰዓት የማመንጨት አቅም አለው ተብሏል።
ሀገሪቱ ለዚህ ግዙፍ የሀይል ማመንጫ ግንባታ 254 ቢሊዮን ዩዋን ወይም 35 ቢሊዮን ዶላር ወጪ እንደምታደርግ ተገልጿል።
በዚህ ፕሮጀክት ምክንያትም 1 ነጥብ 4 ሚሊዮን ቻይናዊያን ይፈናቀላሉ የተባለ ሲሆን ነዋሪዎቹን መልሶ ለማቋቋም 8 ቢሊዮን ዶላር ወጪ እንደሚደረግም ተገልጿል።
እንደ ሽንዋ ዘገባ ከሆነ የሀይል ማመንጫው የሚገነባው ከቻይናዋ ቲቤት ግዛት ተነስቶ ወደ ሕንድ እና ባንግላዲሽ በሚፈሰው ያርሉንግ ዛንግቦ ወንዝ ላይ ይገነባል።
ይህ ፕሮጀክት የግድቡ የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ህዝቦች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያደርስ እንደሚችል ተሰግቷል።
ቻይና በሀይል ማመንጨት አቅሙ በዓለም ቁጥር አንድ የሆነ የሀይል ማመንጫ ባለቤት ስትሆን ስሪ ጎርጅ ሀይል ማመንጫ በዓመት 83ቢሊዮን ኪሎ ዋት ሀይል በማመንጨት ላይ ነው።
አዲሱ የሀይል ማመንጫ የቻይናን ታዳሽ ሀይል አቅም በብዙ እጥፍ እንደሚያሳድገው ተገልጿል።