አሜሪካ ሚሳይል እየሞከረች በነበረበት ወቅት ወደ ጓም ደሴት ለመግባት የሞከሩ ቻይናውያንን በቁጥጥር ስር ማዋሏን አስታወቀች
የጓም ባለስልጣናት ሁሉም የቻይና ዜጎች ከሳይፓን በአንድ ጀልባ መምጣታቸውን እና አሁን ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን ገልጸዋል

የአሜሪካ ባለስልጣናት በደሴቷ ላይ ሊደርስ የሚችል ጥቃትን ለመከላከል የአየር እና የሚሳይል መከላከያ ስርአትን 16 ቦታዎች ላይ ለማጥመድ እቅድ ይዘዋል
አሜሪካ ሚሳይል እየሞከረች በነበረበት ወቅት ወደ ጓም ለመግባት የሞከሩ ቻይናውያን በቁጥጥር ስር ማዋሏን አስታወቀች።
የአሜሪካ ሚሳይል መከላከል ኤጀንሲ የሚሳይል ማክሸፉ ሙከራ እያደረገ በነበረበት ወቅት በህገ ወጥ መንገድ ወደ ጓም ደሴት ለመግባት ሙከራ በማድረግ የከሰሳቻቸውን ሰባት ቻይናውያን በቁጥጥር ስር ማዋሏን የደሴቷ የከስተም እና ኳራንቲን ኤጀንሲ አስታውቋል።
ኤጀንሲው ታህሳስ 10-11 ባለው ጊዜ ከተያዙት ውስጥ ቢያንስ አራት ሰዎች ወታደራዊ መሳሪያዎች ባሉበት ግቢ ተገኝተዋል ብሏል።
ጓም የታህሳስ 10ሩ የሚሳይል ማክሸፍ ሙከራ የተካሄደበትን ጨምሮ በርካታ ወታደራዊ ይዞታዎች (ኢንስታሌሽን) ይገኙባታል።
"በተለይ ሚሳይል ማስወንጨፍ የሚችሉ ይዞታዎች ያሉባቸውን የአሜሪካ ተቋማት መሰለል ለቻይና ዋጋ ያለው መረጃ ሊሆን ይችላል" ሲል የጦር ጥናት ተቋም በትናንትናው እለት ባወጣው ሪፖርት ይፋ አድርጓል።
የጓም ባለስልጣናት ሁሉም የቻይና ዜጎች ከሳይፓን በአንድ ጀልባ መምጣታቸውን እና አሁን ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን ገልጸዋል።
ሮይተርስ የቻይና የውጭ ጉዳይ ዙሪያ ሚኒስትር በጉዳዩ ምላሽ እንዳልሰጠው ገልጿል።
የአሜሪካ ባለስልጣናት በደሴቷ ላይ ሊደርስ የሚችል ጥቃትን ለመከላከል የአየር እና የሚሳይል መከላከያ ስርአትን 16 ቦታዎች ላይ ለማጥመድ እቅድ ይዘዋል። እጅግ ዘመናዊ የአሜሪካ የሚሳይል መከላከያ ስርአትን እና ራዳሮችን ያቀናጃል የተባለው በቀጣይ አስር አመት የሚተገበረው እቅድ 10 ቢሊዮን ዶላር ይፈጃል ተብሏል።
ባለፈው ታህሳስ 10፣2024 የተካሄደው ሙከራ ስኬታማ መሆኑን የገለጸው የሚሳይል መከላከያ ኤጀንሲው በየአመቱ ሁለት የማክሸፍ ሙከራ ሊካሄድ ይችላል ብሏል።