በአሜሪካ የተገኙት ሚስጥራዊ የቻይና ፖሊስ ጣቢያዎች
በኒውዮርክ ከ2022 ጀምሮ ስራ ላይ ነበር የተባለው ፖሊስ ጣቢያ በቻይና የህዝብ ደህንነት ሚኒስቴር የተደራጀ ነው ተብሏል
ቤጂንግ ከአሜሪካ ባሻገር በ53 ሀገራት ዜጎቿን ለመከታትል እና ለማስፈራራት 100 ድብቅ ፖሊስ ጣቢያዎችን እንዳቋቋመች ተሰምቷል
የአሜሪካ ዜግነት ያለው ግለሰብ በኒውዮርክ ከተማ በቻይና መንግስት የተቋቋመ ድብቅ ፖሊስ ጣbiያን በማስተዳደር ተከሷል፡፡
ቼን ጂንፒንግ የተባለው አሜሪካዊ ከሌላ አንድ የስራ አጋሩ ጋር በመሆን በማንሀታን ቻይና ታውን ከሁለት አመታት በላይ ድብቅ ፖሊስ ጣbiያውን ሲያስተዳድሩ መቆየታቸውን በአቃቤ ህግ የክስ ምዝገብ ላይ ተጠቅሷል፡፡
ቤጂንግ አሜሪካን ጨምሮ በ53 ሀገራት 100 ተመሳሳይ ፖሊስ ጣbiያዎችን በድብቅ ማደራጀቷን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ዘገባው ፖሊስ ጣbiያዎቹ በዋናነት የመንግስት ተቃዋሚዎችን እንዲሁም የዴሞክራሲ አቀንቃኝ ቻይናውያንን መከታተል እና ማስፈራረት ላይ የሚሰሩ መሆናቸውን አስነብቧል ፡፡
ጉዳዩን ያስተባበለችው ቻይና ፖሊስ ጣቢያ የተባሉት ቢሮዎች በውጭ ሀገራት ለሚኖሩ ዜጎች አስተዳደራዊ አገልግሎቶችን ለማቅረብ የተመሰረቱ ናቸው ብላለች፡፡
የአሜሪካ ፍትህ ሚኒስቴር ምክትል ጠቅላይ አቃቤህግ ማቲው ኦልሴን ድርጊቱ የአሜሪካ ሉአላዊነትን የጣሰ እና የዜጎችን ደህንነት አደጋ ላይ የጣለ ከፍተኛ ጥፋት ነው ሲሉ አብራርተዋል፡፡
በቻይና የሀገር ውስጥ ደህንነት ሚኒስቴር የተቋቋሙ ናቸው የተባሉት እነኚህ ድብቅ ፖሊስ ጣቢያዎች አስተዳደራዊ አገልግሎቶችን ለመሰጠት የተከፈቱ ናቸው ይባል እንጂ ይፋዊ የስራ ሰአት የሌላቸው እና የአሜሪካ ዜግነት ባለቸው ግለሰቦች የሚመሩ ናቸው ተብሏል፡፡
የአሜሪካ የፌደራል የወንጀል ምርመራ ቢሮ (ኤፍቢአይ) በኒውዮርክ የሚገኘውን ጣቢያ በሀላፊነት ሲመራ ነበር የተባለው ቼን ጂንፒንግ እና የስራ አጋሩ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከመዋላቸው በፊት ከቻይና የሀገር ውስጥ ደህንነት ሚኒስቴር ጋር ሲያደርጉት የነበረውን የጽሁፍ መልዕክት ልውውጥ ከስልካቸው ላይ እንዳጠፉት ደርሰንበታል ብሏል፡፡
ከዚህ ባለፈም በዋናነት በመንግስት የሚፈለጉ ግለሰቦችን፣ ተቃዋሚዎችን ጨምሮ ከቻይና መንግስት በሚላክላቸው የስም ዝርዝር መሰረት ሰዎችን አፈላልጎ በማግኘት ዛቻ እና ማስፈራሪያዎችን ማድረስ ላይ ይሰሩ እንደነበር ተገልጿል፡፡
ግለሰቦቹ በድብቅ ስለላ በቀረበባቸው ክስ ጥፋተኛ መሆናቸውን አምነዋል፤ ይህን ተከትሎም እስከ አምስት አመት ድረስ እስር ይጠብቃቸዋል ተብሏል፡፡